ሀገሬ ቲቪ

ፍሬያማ ውይይት አደረኩ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪካ ኅብረት መስራች እንደመሆኗ ሉኣላዊነቷ በፅኑ መከበር አለባት ተባለ፡፡ ይህንን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከከፍተኛ የዓለም መንግሥታት መሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት ነው፡፡ ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታትና የአፍሪካ ኅብረት መስራች እንደመሆኗ ሉኣላዊነቷ በፅኑ መከበር እንዳለበት ከመንግሥታቱ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማህማት እና ከአውሮፓ ኅብረት ካውንስል ፕሬዝዳንት ቻርልስ ሚሼል ጋር በስልክ ሲወያዩ አፅንኦት እንደሰጡ ተናግረዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ትላንት ማምሻውን ከጅቡቲ፣ ኬንያ፣ ዩጋንዳ፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ከደቡብ ሱዳን መሪዎች ጋር ጥልቅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አሳውቀዋል፡፡ በተጨማሪም ወደ 1.3 ቢልዮን የሚጠጋ ሕዝብ ያላት አህጉር በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ድምጽ እና መቀመጫ እንደሚያስፈልጋት የአፍሪካ መሪዎች የጀመሩትን ጥሪ ተቀላቅያለሁ ማለታቸው በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን አግኝቷል፡፡ ከዓለም መንግሥታት መሪዎች ጋር ያደረጉት የዛሬውንም ውይይት ፍሬያማ እንደነበር አንስተዋል፡፡

በሀገሬ ቴቪ
2021-12-09