ሀገሬ ቲቪ

ኪሳራ የደረሰበት መንግሥት

መንግሥት የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት 124 ቢሊየን ብር ኪሳራ ደርሶብኛል አለ፡፡ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በተደረገው ጥረት በአሁኑ ወቅት መንግሥት 124 ቢሊየን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት አስታውቋል፡፡

የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በሚያዚያ ወር ከ12.8 ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ መደረጉ አይዘነጋም ፡፡ ዘርፉ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የውጪ ምንዛሪ ትልቅ ድርሻ አለው፡፡ ችግሩን ለመፍታት የግብይት ሥርዓቱን ማዘመን ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው ተብሏል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-26