ሀገሬ ቲቪ

ያየለው የጋዜጠኞች እስር

የፍትሕ መጽሔት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዛሬ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰምቷል፡፡ ዓለም አቀፍ የጋዜጠኞች መብት ተሞጋች ድርጅትን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ እና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እየታፈኑ ያሉ ጋዜጠኖች እንዲፈቱ ማሳሰቢያ በተሰጠ ማግስት ነው ጋዜጠኛው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም ታሪኩ ደሳለኝ ለዶቼቬለ እንደገለጸው የጋዜጠኛው የሥራ ባልደረቦች በሁለት መኪና የመጡ ሲቪል የለበሱና የፀጥታ ኃይሎች ነን ያሉ ሰዎች ይዘውት ሄደዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከመጽሔት ሥራው ጋር በተገናኘ ከዚህ ቀደም ታስሮ መለቀቁ ይታወሳል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-26