ሀገሬ ቲቪ

የደንብ ማስከበር እርምጃ

የየካ ክ/ከተማ ደንብ ማስከበር “ህገወጥነትን በጋራ እንከላከል” በሚል መሪ ቃል በ10 ወራት የተከናወኑ ተግባራትን ለህብረተሰቡ ለማሳወቅ የፎቶ አውደርእይ አዘጋጅቷል።

ጽህፈት ቤቱ በ10 ወራት ባከናወናቸው ስራዎች በ 610 የመሬት ወረራ እና የመሬት ማስፋፋት ፣658 ህገወጥ ግንባታ ፣በ 5819 ህገወጥ የጎዳና ንግድ ፣ በ23ሺሕ 200 በሚሆኑ ህገወጥ የመንገድ ማስታወቂያዎች ላይ እርምጃ የወሰደ ሲሆን በአጠቃላይ በተወረሱ ንብረቶች ሽያጭ 2 ሚሊዮን 6መቶ ሺሕ ብር ለፋይናንስ ገቢ ተደርጓል። ይህም የመንገድ ላይ ንግዶች በታሰበው ልክ ባይቀንሱም ህገወጥ የመሬት ወረራዎችን መቆጣጠር ችለናል ሲሉ የየካ ክፍለ ከተማ ደንብ ማስከበር ፅህፈት ኅላፊ ኮማንደር አስፋው የሺዳኝ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ እነዚህ ውጤቶች የመጡት ወደተለያየ ስፍራ በተሰማሩ ደንብ አስከባሪ አካላት መሆኑ ይታወቃል። ነገር ግን እነዚህ ደንብ አስከባሪዎች “እኛ የምንሰራው ህግ ለማስከበር እንዲሁም ከተማችንን ውብና ፅዱ ለማድረግ ቢሆንም ማህበረሰቡ ግን አልተረዳንም በስራችን ላይ እንቅፋት እየሆነ ነው።” ሲሉ ቅሬታቸውን አሰመትዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-05-26