የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህጋዊ የሆነው መጂሊስ በማያውቀው መልኩ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ተቃወመ፡፡
የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጂ ኡመር እድሪስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በብዙ ጥረቶች አንድነት የፈጠረው ሕዝበ ሙስሊሙ ዳግም የመከፈል ችግር ተጋርጦበታል ብለዋል፡፡
በተለይ ህጋዊ የሆነው መጂሊስ በማያውቀው መልኩ ትላንት ‹‹የሰለፊ ውሀብያው›› ያሉት ቡድን በሸራተን ውይይትና ምርጫ ማካሄዱን አውግዘዋል፡፡
ቡድኑ ያካሄደው ውይይትና ምርጫ በምክር ቤቱ እውቅና እንደሌለው ገልጸዋል ፤ የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሁም መላው ኢትዮጵያዊያንና መንግሥት እወቁልኝ ብለዋል፡፡
ሁለት ሙስሊም ታይቶ አይታወቅም ያሉት የምክር ቤት ፕሬዝዳንት አንድነታችንን አጠናክረን ሀገራችንን ከድህነት እናውጣ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-27
