ጆሞ ኬንያታ በኬንያ የነጻነት እና የአፍሪካዊነት እንቅስቃሴ የመሪነት ሚና ተጫውተዋል። ለኬንያ ነጻነት ስላደረጉት እንቅስቃሴም ለዘጠኝ ዓመታት በእንግሊዝ የቅኝ ግዛት አስተዳደር በእስር ቆይተዋል። ከእስር ከተለቀቁ ከሁለት ዓመታት በኋላ ኬንያ ነጻነቷን አገኘች። ጆሞ ኬንያታም በዛሬዋ እለት ከ59 ዓመታት በፊት የነጻዋ ኬንያ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆኑ፡፡ጆሞ ኬንያታ የተወለዱት በምስራቅ አፍሪካ ከፍተኛ ቦታዎች በደቡብ ምእራብ የኬንያ ተራራ ነው፡፡ በ1880ዎቹ መጨረሻ፡፡ ከኩኩዩ ማህበረሰብ የተገኙት ኬንያታ ከሚሽነሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል ችለዋል፡፡
በፈረንጆቹ 1920 ኬንያ የእንግሊዝ ቅኝ ግዛት ሆናለች፡፡ ኬንያታ በቅኝ ግዛት ማእከሏ ናይሮቢ መኖር ጀምረዋል። ኬንያታ የአፍሪካዊነት ንቅናቄዎች ላይ መሳተፋቸውን ቀጥለዋል። ኋላም የኩኩዩ ማእከላዊ ማህበር ዋና ጸሃፊ መሆን ችለዋል። ይሄው ማህበር የአውሮፓውያን ሰፋሪዎችን የጎሳዊ መሬቶችን መውረስ ተቃውሟል፡፡
በፈረንጆቹ 1929 የቅኝ ግዛት ፖሊሲን ለመቃወም ኬንያታ ወደ እንግሊዝ ለንደን ቢያቀኑም ባለስልጣናቱ ግን ሊያገኟቸው ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ፡፡ ኬንያታ የአፍሪካውያንን የመብት ቅሬታ ለማሰማት ወደ ለንደን ብዙ ጊዜ ተመላልሰዋል። በእንግሊዝም በተለያዩ ተቋማት የሞስኮ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ መደበኛ ትምህርትን ተከታትለዋል።
‘Facing Mount Kenya’ የተሰኘ የኩኩዩ ማህበረሰብ ላይ ያተኮረ እና በቅኝ ግዛት ስር ስላለው ችግር የሚጠቁም መጽሃፍ አሳትመዋል። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት በእንግሊዝ በመጻፍ እና በማስተማር አሳልፈዋል።
ኋላም በፈረንጆቹ 1946 ወደ ኬንያ በመመለስ አዲስ የተቋቋመው የኬንያ አፍሪካ ህብረት (KAU) የተሰኘው ማህበር ፕሬዝዳንት ሆነዋል። የብዙሃኑ ድምጽ ህግ እንዲሆንም ግፊት አድርገዋል።ኩኩዮዎች እና ኩኩዮዎች ያልሆኑትን ለጸረ አመጽ እንቅስቃሴ መልምለዋል።
በፈረንጆቹ በ1952 የኩኩዩ ጽንፈኛ ቡድን የሆነው ማኡ ማኡ በነጭ ሰፋሪዎች እና በቅኝ ገዥው አስተዳደር ላይ የሽምቅ ውጊያ ከፈተ። ይህም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኩኩዮዎች ወደ እስር ካምፖች እንዲገቡ አድርጓል። በአመጹ የኬንያታ ሚና ብዙም ባይሆንም በእንግሊዞች ተሰድበዋል። ከሌሎች አምስት የኬንያ አፍሪካን ዩንየን መሪዎች ጋር የማኡ ማኡ ሽብርተኛ ቡድንን በማስተዳደር በሚል ክስ ተመስርቶባቸዋል።
የሰባት ዓመት እስር የተፈረደባቸው ኬንያታ ሲዲስት አመታትን በእስር ካሳለፉ በኋላ በሎድዋር ወደ ሚገኝ የውስጥ ግዞት ተላኩ። በዚያም የቁም እስረኛ ሆኑ። ኋላም ቀስ በቀስ የእንግሊዝ መንግስት የኬንያ አስተዳደርን ወደ ጥቁሮች አብላጫ አገዛዝ መምራት ጀመረ።
በምዕራባውያን በ1960 በጥቁር ብሄርተኞች የተቁቋመው የኬንያ አፍሪካን ናሽናል ዩንየን(KANU) ኬንያታን በሌሉበት ፕሬዝዳንት አድርጎ መረጣቸው። KANU ኬንያታ እስካልተፈቱ በየትኛውም የመንግሥት እንቅስቃሴ ላይ እንደማይሳተፍ አስታወቀ።
በቁም እስር ላይ የነበሩት ኬንያታ ተፈቱ። በኬንያ የሚገኙ ሰፋሪዎችን ደህንነት ለመጠበቅም ቢሆን ቃል ከመግባት አልሰነፉም።
ስለ ኬንያ ነጻነት ለመደራደርም ወደ ለንደን ተጉዘዋል። በዛሬዋ እለት በፈረንጆቹ 1963 ደግሞ በሌሉበት መርጦ ፕሬዝዳንት ያደረጋቸውን ኻኑን የቅድመ ነጻነት ምርጫ አሸናፊ አድርገውታል። ኬንያ በይፋ ነጻ ከሆነች በኋላ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስተር በይፋ ተብለዋል። ኬንያ ህገ መንግስቷን አጽድቃ ሪፐብሊክ ከተባለች በኋላ ኬንያታ የተመረጡ ፕሬዝዳንት ሆነዋል።
በፈረንጆቹ 1978 እስኪያርፉ የኬንያ መሪ የነበሩት ኬንያታ የኬንያ መስራች አባት ተደርገው የሚታሰቡ ሲሆን በአፍሪካ ተጽእኖ ፈጣሪ ሆነው ካለፉ መሪዎች አንዱ ናቸው።
በአብርሃም በለጠ
2022-05-27
