ሀገሬ ቲቪ

የታክሲ አገልግሎት የጀመረው ኢቲ ታክሲ

ኢቲ ታክሲ አገልግሎት መስጠት ጀምሬያለው አለ።

ኢቲ ታክሲ በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ አቅምን ያገናዘበ አገልግሎት ልሰጥ ተዘጋጅቻለውም ነው ያለው።

በኬቢ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር ባለቤትነት የሚተዳደረው ኢቲ ታክሲ ተጠቃሚዎች አገልግሎቱን የሚያገኙበትን የሞባይል መተግበሪያ ይፋ አድርጓል። መተግበሪያው በተሻለ ፍጥነት አገልግሎት ለመስጠት እንዲያስችል ተደርጎ መዘጋጀቱንም ሰምተናል።

እንዲሁም ተጠቃሚዎች በተሻለ መተማመን አገልግሎቱን እንዲያገኙ በማሰብም ጉዞው ከጀመረበት ደቂቃ ጀምሮ በመተግበሪያው ላይ ለአሽከርካሪውም ለተሳፋሪዎም ማሳየት እየተጓዙ ያሉበትን ርቀት እየቆጠረ ማሳየት እንዲችል መደረጉንም በማብሰሪያ ፕሮግራሙ ላይ ሰምተናል።

ከዚህ በተጨማሪም ኢቲ ታክሲ ለተጠቃሚዎች በተጓዙበት ርቀት ልክ ከሞባይል ስልክ ጀምሮ በርካታ ሽልማቶችን የሚያስገኙ እጣዎችን ለተጠቃሚዎቼ አቅርቤያለው ብሏል።

አሽከርካሪዎችም ቢሆኑ ባደረጓቸው ጉዞዎች ልክ የተሻለ ተጠቃሚ የሚሆኑበትንም አገልግሎት አልረሳንም ብለዋል።

ለሚቀጥሉት 3 ወራትም አሽከርካሪዎች ከኮሚሽን ነጻ አገልግሎቱን መስጠት እንደሚችሉም በማብሰሪያ መድረኩ ላይ ተሰምቷል። ድርጅቱ ኢቲ ታክሲን የሚወክሉ ብራንድ አምባሳደሮችንም መርጧል።

ለመጀመሪያ ዙር ለተጠቃሚዎች ያስመጣቸውን ዘመናዊ መኪኖክንም በይፋ አስመርቆ ወደ ስራ መግባቱን አብስሯል።

በሳምሶን ገድሉ
2022-05-27