ሀገሬ ቲቪ

የቁርአን ውድድር በሀገራችን

በኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የቅዱስ ቁርዐን ውድድር ሊዘጋጅ ነው። ከሰኔ 1 እስከ ሰኔ 5 የሚደረገውን ዓለም ዓቀፍ የ ቅዱስ ቁርዐን ውድድር በማስመልከት ዛሬ በሸራተን ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።

ውድድሩ ከ 56 የዓለማችን ሀገራት የተወጣጡ ተወዳዳሪዎችን ተሳታፊ የሚያደርግ ሲሆን ከ100 በላይ ሀገራት ዜጎች ለዚሁ ዝግጅት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ በመግለጫው ተገልጿል።

ይህ ውድድር ተተኪው ትውልድ በቅዱስ ቁርዐን ላይ ያላቸውን ዕውቀት ከማጎልበት በላይ ለሀገራችን የሚያበረክተው ማኅበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ አስተዋፆው ከፍተኛ ነው ተብሏል።

የተለያዩ ሀገራት ውድድሩን ቀደም ብለው ያካሔዱ ሲሆን በኢትዮጽያ የሚደረገውን ውድድር የሚካፈሉት በሀገራቸው የተደረገውን ውድድር በአንደኝነት ያጠናቀቁ ብቻ ናቸው ተብሏል።

የአሸናፊዎች አሸናፊ የሚሆነው እስከ 1 ሚሊዮን ብር ሽልማት እንደሚሸለም ኡስታዝ ኑረዲን ቃሲም ነግረውናል።

ይህ ዝግጅት ከ ሀይማኖታዊ ይዘቱ ባሻገር ከተለያዩ ሀገራት ከሚመጡ ዜጎች ለሀገር የውጭ ምንዛሬን በማምጣት እንዲሁም የቱሪስት መስዕብ የሆኑ ቦታዎችን በማስጎበኘት ያለው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳው የጎላ ነውና የሚመለከታቸው አካላት ዝግጅቱን በመደገፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-05-27