ሀገሬ ቲቪ

የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በጊኒ

የአፍሪካ ህብረት በአህጉሩ ያጋጠሙ ሰብዓዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶች ላይ የሚያተኩር ጉባኤ በኢኳተርያል ጊኒ ማላቦ እያካሄደ ነው።

በኢኳተርያል ጊኒ የተጠራው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈጻሚዎች አስቸኳይ ጉባኤ በአህጉሩ ያጋጠሙ ሰብዓዊ እና ፖለቲካዊ ቀውሶችን ለመቅረፍ ያለመ ነው ተብሏል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ዋና ኃላፊ የሆኑት ሙሳ ፋኪ መሃመት ከሰሜን አፍሪካ ሊቢያ እስከ ደቡብ አፍሪካ ሞዛምቢክ፣ ከምዕራብ አፍሪካ ማሊ እስከ የአፍሪካ ቀንድ ሶማሊያ፣ ከሳህል ቀጠና የቻድ ተፋሰስ እስከ ምስራቅ ኮንጎ መካከለኛው አፍሪካ ሽብርተኝነት በኢኮኖሚ እና በሰዎች ደህንነት ላይ ተጽእኖ ማሳደሩን ቀጥሏል ብለዋል።

እየተካሄዱ ያሉ መፈንቅለ መንግስቶችም የዴሞክራሲ ግንባታውን ወደኋላ ይመልሱታል ብለዋል።

በአብርሃም በለጠ
2022-05-27