ሀገሬ ቲቪ

‹‹ለመብላት የሚደረግ ትንቅንቅ››

ለመብላት የሚደረግ ትንቅንቅ በየእለቱ ወደ ስራ ሲሄዱ በህይወት ይመለሱ እንደሆነ ምንም አያውቁም፤ ድህነት ከምድር በታች ወርቅ እንዲፈልጉ ያስገድዳቸዋል፡፡ አንዳንዶቹ በህገ ወጥ መንገድ በማዕድን ፍለጋ ይታሰራሉ፤ አንዳንዶቹ ይሞታሉ፡፡

በደቡብ አፍሪካ ህገ-ወጥ ማዕድን ማውጣት በአህጉሪቱ በጣም ትርፋማ ከሚባሉት ውስጥ አንዱ ሲሆን ማዕድን አውጪዎች ህይወታቸውን ለማስቀጠል ጤናን እና ደህንነትን አደጋ ላይ ጥለው ስራውን እንዲጋፈጡ ገፋፍቷቸዋል፡፡

ብዙዎች በዚሁ ስራ ሀብታምም ሆነዋል፡፡ ሀብታም የመሆን እድሉ የማዕድን ቆፋሪዎችን በሚገባ ያነሳሳቸዋል፡፡ ህገወጥ አውጪዎቹ ብዙውን ጊዜ የይገባኛል ጥያቄዎቻቸውን ለመከላከል ሲሉ ብሎም ለደህንነታቸው ሲሉ የታጠቁ ናቸው፡፡

ዛማ ዛማ (ቁማር ተጫዎቾቹ) በሚል ስያሜ የሚጠሩት እነዚህ አውጪዎች አሊያም ማዕድን ቆፋሪዎች አንዳንዶቹ በአንድ ወቅት በህጋዊ የማዕድን ኢንዱስትሪ ውስጥ የሰሩ በመሆናቸው ለመጋፈጥ ሆነ ብለው የወጡ ናቸው፡፡

መደበኛ ያልሆኑ ማዕድን አጥማጆች፣ ብዙዎቹ ከዚምባብዌ ወይም ከማላዊ የመጡ ስደተኞች ራሳቸውን ዛማ ዛማ ብለው ይጠሩታል፣ ትርጉሙም “መሞከርን የሚቀጥሉ ሰዎች” ነገር ግን ነገሮችን አደጋ ላይ የሚጥሉ ሰዎችም ጭምር ነው ይላሉ፡፡

ድህነት እና ተስፋ መቁረጥ እንደ ዮሴፍ ያሉ አንዳንድ ደቡብ አፍሪካውያን ወርቅ ለማግኘት በማሰብ ህይወታቸውን እንዲያጡ እየገፋፋቸው ነው፡፡

ጆሴፍ በዚህ ስራ የተሰማራ ወጣት ነው በጥንቃቄ እንዳይገደል በመፍራት ከመሬት በታች እየቆፈረ ቤተሰብ ያስተዳድራል፡፡

“ምንም እንኳን ያሉት ሁኔታዎች አደገኛ ቢሆኑም እየቆፈርንና እያቀነባበርን ለቤተሰቦቻችን እንተርፋለን፡፡ አቧራና ኬሚካል ተደባልቆ ጤናችን አደጋ ላይ መውደቅን ጨምሮ በአደገኛ አካባቢዎች እየሠራን ነው፡፡በጣም ከባድ ነው፡፡ከጠዋት ጀምሮ እስከ ፀሐይ መግቢያ ድረስ እንሰራለን እና አንድ ግራም ወርቅ ለማምረት አንዳንድ ጊዜ አንድ ወይም ሁለት ቀን በጉድጓድ ውስጥ ማሳለፍን ይጠይቃል፡፡”

ለቤተሰብ አስተዳዳሪው ዮሴፍ ይህ የእሱ ብቸኛ የመዳን ምንጭ ነው፡፡

ጄምስ ዌለስተድ ከደቡብ አፍሪካ ትልቁ የወርቅ አምራች ኩባንያ የሆነው ሲባኒ ስቲልዎተር ውስጥ ምክትል ዳይሬክተር ናቸው፡፡

“የማዕድን ዘርፉ ከብዙ ዓመታት በፊት በደቡብ አፍሪካም በጣም እየቀነሰ እንደመጣ ታውቃላችሁ፣ ይህ ማለት ብዙ የቀድሞ ማዕድን አጥኚዎች አሉ፣ አሁን ስራ የላቸውም፣ ስለዚህም አንዳንዶቹ ወደ ህገወጥ ማዕድን ማውጣት ስራ ይሰማራሉ፡፡ ለማዕድን ኢንዱስትሪውም ሆነ ለሀገሪቱ በአጠቃላይ ትልቅ ፈተና ነው” ብለዋል፡፡

በሚገርም ሁኔታ ሕገ-ወጥ ማዕድን ቆፋሪዎች የፖሊስ ጥቃት ሲደርስባቸው ለማስጠንቀቅ እና ተቀናቃኝ የማዕድን ቆፋሪዎችን ለመከላከል የራሳቸውን የጥበቃ ሠራተኞች ቀጥረዋል፡፡

የእነዚህ ቆፋሪዎች የደህንነት ጠባቂ የሆነው ሴሌምባ ልክ እንደ ማዕድን አውጪዎች፣ ቤተሰቡን ለመንከባከብ ጥቂት አማራጮች እንዳሉት ይናገራል፡፡

“ማንም ሰው ወደ ዘንጉ በወረደ ቁጥር ግለሰቡ አንድ ነገር መክፈል አለበት፡፡ ማዕድን አውጪው ሲወጣ ሲገባ እኔ አለሁ፡፡ እኛ በፈረቃ እየሰራን ነው ፣ እያንዳንዱ ቡድን በሳምንት ሁለት ምሽቶች ይሰራል በዚህ መሰረት ነው ጥበቃ የምናደርገው፡፡”

ነገር ግን ቬለስተድ ዛማ ዛማዎች የራሳቸውን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥሉ ብቻ አይደሉም በጣም ጥንቁቆች ናቸው ይላሉ፡፡

“ብዙውን ጊዜ የታጠቁ ናቸው፡፡ስለዚህ ለሰራተኞቻችን ስጋት አለ፣ ህገ-ወጥ ማዕድን ቆፋሪዎች ከመሬት በታች እየሮጡ ከሆነ ድርሽ ማለት አንችልም፡፡የሰራተኞች ሙስና እና ማጭበርበር ከዚህ ጋር ዝምድና አለው፡፡ ይህ ህገወጥ የማዕድን ማውጣት በግልፅ ይታወቃል፤ የእኛ የሆኑትን ሀብቶችንም እየዘረፉ ነው፡፡ህጋዊ ሆነን መስራት አልቻልንም ፡፡” ብለዋል፡፡

ሕገ-ወጥ የማዕድን ማውጣት ችግሮችን ለማስወገድ፣ ባለሥልጣናት ለማዕድን ሠራተኞች ተጨማሪ የሥራ አማራጮችን መፍጠር አለባቸው ብለዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የማዕድን ኢንዱስትሪው ካላት 588 ቢሊዮን ዶላር አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት 18 በመቶውን ይሸፍናል፡፡ ነገር ግን ህገወጥ ማዕድን ማውጣት እና ተያያዥ የወንጀል ድርጊቶች እንደ የታክስ ማጭበርበር፣ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና የስደተኞች ዝውውር የኢንዱስትሪውን ጥቅም እየሸረሸሩ ነው፡፡

ይህ የደቡብ አፍሪካ ችግር ብቻ አይደለም መለስ ብለን የቤታችንን ጎዳ መመልከቻ መነጽር እንጂ፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-30