በመዲናችን አዲስ አበባ የሚስተዋለው የህገ ወጥ ማስታወቂያ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአይነትም ሆነ በመጠን እየጨመረ ነው። ይህ ድርጊት በከተማው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ልማታዊ እንቅስቃሴ ባስ ሲልም በከተማዋ ገጽታ ላይ አሉታዊ ጥላውን እያጠላ ነው።
አሁን አሁን የሚስተዋሉት ማስታወቂያዎች በአደባባይ የሚለጠፉ፣ ርቀታቸውን ያልጠበቁ ፣መጋቢ መንገዶች ላይ የሚተከሉ ፣ የእግረኛን እንቅስቃሴ የሚዋኩና የአረንጓዴ ቦታዎች መከለያ ላይ የሚተከሉ መሆናችው ግልጽ ነው።
ለዚህም ይመስላል የአዲስ አበባ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከባለድርሻ አካላት ጋር በህገ-ወጥ ማስታወቂያ መከላከል ዙርያ የመከረው ። በውይይቱም የውጪ ማስታወቂያ ባለሙያዎች ተገኝተው በዘርፉ በሚታዩ ጉድለቶች ዙሪያ ቅሬታ አቅርበዋል። እንደ ማስታወቂያ ድርጅቶቹ የተወሰኑ ቡድኖች ብቻ ናቸው ዘርፉንን ጠቅልለው የያዙት ፣ የመዲናዋ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን የማስታወቂያ ድርጅቶችን ህጋዊ ለማድረግ በሚያደረግው አካሄድ ማስታወቂያዎች የሚፈርሱም ከሆኑ ያለልዩነት ይፍረሱና ሊሎችም ቅሬታዎች ተነስተዋል።
የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ የአብነህ ገዳሙ በመዲናዋ በደንብ ማስከበር ባለሙያዎች የምታዩትን የስነምግባር ጥሰቶች በነጻ የስልክ ቁጥራችን ልትጠቁሙን ትችላላችሁ ብለዋል።
የመዲናዋ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን ዳይሬክተር ኢንጅነር ስጦታው አካለ በበኩላቸው የውጪ ማስታውቂያ ፈቃድ አስጣጡ የሚመራበት አስራር የለውም የተባለውን እንደማይቀበሉ ጠቅሰው እንዳንድ የማስታወቂያ ባለሙያዎች ከተማው ሲዘምን ከሲስተም እንደሚወጡ ቀድመው አውቀዋል ብለዋል።
ኢንጅነር ስጦታው ማኅበሩ አንድ ሆኖ ወደ ተቋማችን መምጣት አለበት እኛም እንደ ተቋም ሰራተኞችቻንን ገምግመን እርምጃ እንወስዳለን ብለዋል።
በቀጣይ ህገ ወጥ ማስታወቂያ የሚተክሉ ፣ የሚያሰርጩ ና የሚያንጠለጥሉ ድርጅቶችን በአድራሻቸው ተጠያቅ እንደማደርግ እወቁልኝ ብሏል።
የመዲናዋ ዲዛይንና ግንባታ ቁጥጥር ባለስልጣን በቀጣይ የውጭ ማስታወቂያ ፈቃድ ያላቸውን ሁሉንም ድርጅቶች ዳግም ለመመዝገብ ውጥን ይዟል።
ከዚህ ቀደምም ሀገሬ ቴሌቭዥን በዚሁ በህገወጥ ማስታወቂያ ጉዳይ የሚመለከታቸውን አነጋግሮ ዘገባ መስራቱ ይታወሳል ።
በመቅደስ እንዳለ
2022-05-30
