የዛሬው እለቱን ከታሪክ ወደ 1960ዎቹ እውቅ የሙዚቃ ባልደረቦች ይወስደናል። ‘The Beatles’ ይሰኛሉ። በፈረንጆቹ 1960 በእንግሊዝ ሊቨርፑል የተመሰረተ የሮክ ባንድ ነው። የምንጊዜም ተጽእኖ ፈጣሪ ባንድ ዝርዝር ውስጥ ስማቸው ይጠቀሳል። የዚሁ ባንድ አባላት ለ20 ሳምንታት በስቱድዮ እንዲያሳልፉ ያደረጋቸውን ‘White Album’ ን መስራት የጀመሩት በዛሬዋ እለት ከ84 አመታት በፊት ነው።
‘The Beatles’ የምንጊዜም ተጽእኖ ፈጣሪ ባንዶች ዝርዝር ውስጥ የማይጠፋ ስም ነው። በ1960ዎቹ እውቅ ሙዚቃዎች ላይ የራሳቸውን አስተዋጽኦ እና ጥበባዊ አሻራ አሳርፈዋል። ጆን ሌኖን፣ ፖል ማካርትኒ፣ ጆርጅ ሃሪሰን እና ሪንጎ ስታርን ያቀፈ የሮክ ባንድ ነው።
ይሄው ተጽእኖ ፈጣሪ ሆኖ መውጣት የቻለው ባንድ አራቱ ሙዚቀኞች በሊቨርፑል በጋራ በመጫወት የጀመሩት ነው።
አራቱ ሙዚቀኞች በጋራ ከመጣመራቸው አስቀድሞ ተራ አፍላ ወጣቶች ነበሩ። ማንም የአለም ተጽእኖ ፈጣሪ ባንድ ባለቤት ይሆናሉ ብሎ የጠበቀም አልነበረም።
በጥምረት መስራት ሲጀምሩ ግን በሙዚቃ ፈጠራ ስራዎቻቸው ጆሮዎችን መያዝ ቻሉ።
በሙዚቃው ዘርፍ በግጥሙም፣ በዜማውም፣ በአቀራረብ ፈጠራቸው ፈር ቀዳጅ መሆን የቻሉት ቢትልስ የዘመኑ የወጣቶች እና ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴ መሪዎች ተደርገው ይታዩ ነበር።
አራቱን ሙዚቀኞች ያቀፈው ባንድ የሙዚቃ ግጥም ጸሃፊ በነበሩት ሌኖን እና ማካርትኒ የሚመራ የነበረ ሲሆን ከሌነን የቀድሞ ቡድን ‘The Quarymen’ የወጣ ነው። በሊቨርፑል እና ሃምበርግ ከፈረንጆቹ 1960 ጀመሮ ላሉት ሶስት አመታት ሙዚቃዎችን በምጫወት ዝናቸውን ከፍ ማድረግ ችለዋል።
በእንግሊዝ በመጫወት ዝናን ማትረፍ የቻሉት የ’The Beatles’ አባላት ‘Love Me Do’ የተሰኘ የሙዚቃ ስራቸውን ከለቀቁ በኋላ በኢንግላንድ የነበራቸው እውቅና ይበልጥ ከፍ ብሏል።
ለስቱድዮ ስራዎች ሰፊ ጊዜ በመስጠትም ከመድረክ ስራዎች በመራቅ ብዙ የስቱድዮ የፈጠራ ሙዚቃዎችን ማበርከት ችለዋል።
እ.ኤ.አ. በ1964 የእንግሊዝ የፖፕ የሙዚቃ ገበያ ወረራን በመምራት አለም አቀፋዊ ኮከብ መሆን ችለዋል።
አለም አቀፍ እውቅናን ማትረፍ የቻሉት ዘ ቢትልስ ምርጥ ስራዎችቻቸውን ከፈረንጆቹ 1965 ጀምሮ ለጆሮ አብቅተዋል። ፈጠራ የታከለበት እና ሰፊ ተወዳጅነት ያገኘላቸውን ‘Rubber Soul’ (1965) ጨምሮ ‘Revolver ‘(1966) )፣ ‘Sgt. Pepper's Lonely Hearts Club Band ‘(1967) ፣’The Beatles /The White Album’(1968) እና ‘Abbey Road ‘(1969) የተሰኙ አልበሞቻቸውን ለአድማጮቻቸው ማድረስ ችለዋል።
ዘ ቢትልስ በአለም አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊዮን ያክል የሙዚቃዎች ሽያጭ በማግኘት በአለም አቀፍ ደረጃ የምንጊዜም በብዛት የተሸጡ የሙዚቃ ስራዎች ባለቤት ናቸው። በእንግሊዝ የምንጊዜም አልበሞች ሰንጠረዥ ተቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ።
በእንግሊዝ 29.1 ሚሊዮን የነጠላ ዜማዎች ሽያጭ ተቀዳሚውን ቦታ ይይዛሉ። ዘ ቢትልስ ሰባት የግራሚ አዋርድ ሽልማቶችን፣ አራት የብሪት አዋርድ ብሎም የአካዳሚ አዋርድን ማግኘት ችለዋል።
በፈረንጆቹ 2004 እና 2011 የ’Rolling Stone’ በታሪክ ውስጥ ታላላቅ ከያኒያን ዝርዝር ውስጥ መካተት ችለዋል።
‘Time’ መጽሄት ደግሞ ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አስፈላጊ ሰዎች አንዱ አድርጎ ያካትታቸዋል።
እ.ኤ.አ. 1970 ዘ ቢትልስ ከመበታተናቸው አስቀድሞ እያንዳንዳቸው የተለያየ የሙዚቃ ስኬትን ማጣጣም ችለዋል።
ማካርትኒ እና ስታር በሙዚቃው በንቃት ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሌነን በፈረንጆቹ 1980 ተተኩሶበት ተገደለ። ሃሪሰንም ቢሆን እ.ኤ.አ. በ2001 በካንሰር ህይወቱ አልፏል።
በአብርሃም በለጠ
2022-05-30
