ሀገሬ ቲቪ

የንባብ ባህል ሳምንት መርሐግብር

አምስተኛው ዙር ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ሳምንት ከግንቦት24 እስከ26 እንደሚካሔድ የአዲስአበባ ባህልኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ተናግሯል። መጽሐፍትን ከአንባቢያን በማገናኘት የትውልዱን የንባብ ባሕል ለማጎልበት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ሳምንት እንዲጀመር ምክንያት ሆኗል።

በዚኽ የንባብ ሳምንት መርሀግብር በርካታ አላማዎች ያሉት ሲኾን አንባቢ ትውልድን መፍጠር አንዱ እንደሆነ የአዲስአበባ ባህልኪነጥበብ እና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ቢሮ ኅላፊ አቶ አስፋው ለገሰ ተናግረዋል።

በአምስተኛው ከተማ አቀፍ የንባብ ባህል ሳምንት 48 ተቋማት እንደሚሳተፉ ነው የተገለጸው። ከነዚህም ውስጥ 22 የሚሆኑት በከተማዋ የሚገኙ መጽሐፍት ሻጮች ሲኾኑ 26ቱ ደግሞ የተለያዩ ቤተ መጽሓፍት ናቸው ተብሏል። ከነዚኽ በተጨማሪ እንደ ወመዘክር እና ብሔራዊ ሙዚየም ያሉ ተቋማት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ነው አቶ አስፋው ለገሰ የተናገሩት።

ከአምስት ወራት በፊት ግልጋሎት መስጠት የጀመረው አብርኆት ቤተ መጽሐፍት በንባብ ረገድ የጎላ ጥቅም እየሠጠ ይገኛል። ለዚሁ ቤተ መጽሐፍት እየተደረገ ባለው መጽሐፍ የማሰባሰብ ሥራ እስካሁ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ መጽሐፍ እንደተሰበሰበ የአ.አ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት አማካሪ ኢንጂነር ውብ አየሁ ማሞ ተነግረዋል። አሁን ላይ በቀን ወደ ላይብረሪው ከ አራት ሺሕ ያላነሰ ሰው እንደሚመጣም ተናግረዋል።

በቀጣይ በኦንላይን ወይም ኢንተርኔትን በመጠቀም ተገልጋዮች ቤታቸው በመሆን ሥለ ቤተ መጽሓፍቱ ሙሉ መረጃ ማለትም ስለመጽሀፍቱ፣ ማንበቢያ ቦታ መኖሩን እና የመሳሰሉትን መረጃ ማግኘት የሚቻልበት አሠራር ይፋ ይሆእናልም ተብሏል።

በሙሉጌታ በላይ
2022-05-30