በባለፉት አራት ዓመታት ባንኮች ላይ በሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተነሳ 1.8 ቢሊየን ብር ምዝበራ ማጋጠሙን የፍትህ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከደረሰው ምዝበራ ውስጥ 50 ነጥብ 7 በመቶ ምዝበራው የደረሰው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ ነው ሲሆን በመቀጠል ከፍተኛ ምዝበራ ያጋጠማቸው አቢሲኒያ ባንክ 328.9 ሚሊየን ብር፣ ኦሮሚያ ባንክ 161.8 ሚሊየን ብር እና ወጋገን ባንክ 155.6 ሚሊየን ብር ናቸው፡፡
የፍትህ ሚኒስቴር ዲኤታ ፍቃዱ ፀጋ እንደተናገሩት በባንኮች ላይ የሚፈፀሙ የማጭበርበር ወንጀሎች የተለያየ መልክ የሚከተሉ በመሆናቸው የሚያደርሱት ቀውስና አደጋ ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
የማጭበርበር ወንጀሎቹ በባንኮች አስተዳደር አካላት፣ የባንክ ሰራተኞች፣ በሦስተኛ ወገን የሚፈፀሙ ሲሆን በሚፈፀሙት ወንጀሎችም የኢትዮ-ቴሌኮም ሰራተኞች ጭምር መሳተፋቸው በጥናት አመላክቷል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-30
