የመንግሥት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ ያሳድጋል የተባለው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ፡፡
በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባው ማዕከሉን ጠቅላይ ሚኒስትር (ዶ/ር) ዐቢይ አህመድ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ተመርቋል፡፡
ለኩላሊት ህመምተኞች እፎይታን ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀው በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተሰራው የኩላሊት እጥበት ማዕከል ቀድሞ በኹሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-30
