የምርጫ ተወዳዳሪዎች የሰውን ቀልብ ለመሳብ የተለያዩ የምርጫ መቀስቀሻ መንገዶችን ሲጠቀሙ እንሰማለን፡፡ ከወደ ኬንያ ብቅ ያለው ፖለቲከኛ ፕሬዝዳንት ሆኜ ከተመረጥኩ ለአዲስ ሙሽሮች ብድር እሰጣለሁ ሲሉ ቃል ስለመግባታቸው የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን አግኝቷል፡፡ በኬንያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እጩ ተወዳዳሪ ሆነዉ የቀረቡት ፓለቲከኛ በሚቀጥለው ዓመት አጠቃላይ ምርጫ ማሸነፍ ከቻልኩ ለአዲስ ሙሽሮች ከከ4 ሺሕ 400 እስከ 8 ሺሕ 800 ዶላር ብድር እሰጣለሁ ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡ እሁድ እለት የፕሬዝዳንት ማኒፌስቶ ይፋ ያደረጉት የማቻኮስ ገዥ አልፍሬድ ሙቱዋ በ20 ዓመታት ውስጥ በሚከፈል ዝቅተኛ ወለድ ጥንዶች በክብር ህይወት እንዲጀምሩ ይረዳል ይህንንም አደርገዋለሁ ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የዚህ ሁሉ ውጤት ምንድን ነው ካላችሁ ክብር ለሁላችንም ያስፈልጋል የኑሮ ደረጃን ማሻሻል ደግሞም በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ ቤቶች ጥራት በመጨመር የጭቃ ቤቶች እንዳይኖሩ አደርጋለዉ ሲሉ ሙቱዋ ፎክረዋል፡፡ ችግኝ ተከላ ደግሞ እንደ ጥሎሽ ክፍያ እንዲቆጠር መንግሥታቸው እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ሙቱዋ ጥሎሽ ለመክፈል ስትሄዱ ምን ያህል ዛፎች እንደዘራችሁ መናገር ይኖርባችኃል ሲሉም ፖለቲከኛዉ ተደምጠዋል፡፡ ኬንያውያን ግን ፖለቲከኛዉ የሰጡት ሀሳብ ላይ የሰላ ትችት እና ፌዝ ፈጥሮባቸዋል ሲል ስታንዳርድ ኒውስ፡፡ በ10 ዓመታት የስልጣን ዘመናቸው የመጨረሻ ወራት ላይ የሚገኙትን ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታን ለመተካት ወደ አስር የሚጠጉ ፖለቲከኞች ከወዲሁ ዘመቻ ጀምረዋል፡፡ በነሀሴ 2022 ለሚካሄደው ምርጫ እንደ ዋና ተፎካካሪ ከሚታዩት መካከል አንጋፋው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ራይላ ኦዲንጋ እና የወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ይገኙበታል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-07
