ሀገሬ ቲቪ

የኢሰመጉ ዓለምአቀፍ ሽልማት

ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) የ2022 የሰብአዊ መብቶች ሽልማት ከአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሊበረከትለት ነው፡፡

ሽልማቱ ኢሰመጉ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በመሆኑ አንዲሁም የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ህይወት ስጋት ውስጥ በሚከቱ ከባድ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን መስራት በመቻሉ የሚሰጠው እውቅና ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል፡፡

የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳን ይርጋ ከጀርመን ሆነው ጋዜጣዊው መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ዋናው ሽልማት ምርሃ ግብር ከምሽት 3:00 ጀምሮ በቀጥታ ስርጭት የሚከናወን ይሆናል ተብሏል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-30