ሱዳን ከባለፈው ዓመት አንስቶ ጥላው የነበረውን አስቸኳይ አዋጅ አነሳች፡፡
ባለፈው ዓመት በሀገሪቱ መፈንቅለ መንግሥት መደረጉን ተከትሎ የተጣለው አስቸኳይ አዋጅ የሀገሪቱ ጦር መሪ ጀነራል አብዱልፈታ አልቡርሀን ማንሳታቸውን ተገልጿል፡፡
የሀገሪቱ ከፍተኛ የጦር ሹማምንቶች በጉዳዩ ላይ ውይይት አድረገው አዋጁን ተጥሎ በነበረ ወቅት ታስረው የነበሩ ዜጎች እንዲፈቱ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ “በሽግግሩ ወቅት መረጋጋትን የሚያመጣ ፍሬያማ እና ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ የሚያስችል ትክክለኛ ሁኔታ ለመፍጠር ነው” ብሏል፡፡
ሱዳን ከመፈንቅለ መንግሥቱ በኋላ በተቀሰቀሰ ሕዝባዊ ተቃውሞ እየተናጠች ትገኛለች፣በአመጽ የተወሰደ እርምጃ ወደ 100 የሚጠጉ ሰዎችን ህይወት ማጥፋት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል፡፡
በሙሉጌታ በላይ
2022-05-30
