በዩናይትድ ስቴትስ ከተማ የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ ታዋቂ የሆነች አንዲት ደራሲን ባሏን በመግደል ወንጀል ጠርጥሮ ፍርድቤት አቁሟታል። ነገሩ እንዲ ነው ሟች ዳንኤል ብሮፊ በሞያው ሼፍ ሲሆን በደቡብ ምዕራብ ፖርትላንድ በሚገኘው ምግብ ቤት ውስጥ ለማብሰል ሲዘጋጅ ባልታወቀ ሰው ህይወቱ ያልፋል።
የ ሀገሪቱ ፖሊስ የዚህን ሰው ገዳይ ለማግኘት ረጅም ጊዜ ምርመራ ቢያደርግም ጠብ የሚል ነገር ያጣል ።
ታዲያ ፖሊስ በዚህ ሰው ግድያ አንድን ሰው ተጠያቂ ማድረግ አሰበ የሟችን ባለቤት ።
በመቀጠልም የ71 ዓመቷን ደራሲ በባለቤቷ በዳንኤል ብሮፊ ሞት ተጠርጣሪ ነሽ በሚል ፍርድ ቤት ያቆማታል ።
ለምን ተጠረጠርች ቢሉ ፖሊስ እንዲ ሲል ይመልስሎታል ክሪምፕተን ማለትም ተጠርጣሪዋ በ አንድ ወቅት ላይ ባልሽን እንዴት መግደል ትችያለሽ ስትል መጽሀፍ አሳትማ ለገብያ አውላለች።
ደራሲዋ በመጽሀፉ “በፍቅር ስሜት የተረበሽኩ ጸሐፊ በመሆኔ ስለ ነፍስ ግድያና ስለ ፖሊስ አሠራር በማሰብ ብዙ ጊዜዬን አሳልፊያለሁ። ደግሞም ግድያ ብፈጽም እንኳን ነፃ ሊያወጣኝ የሚችሉ ነግሮችን አስቢያልሁ። በእስር ቤት ምንም ጊዜ ማሳለፍ አልፈልግም። ስለዚህ ባል መግደል ለኔ ቀላሉ ነገር ነው። ነገር ግን ሰዎችን ከመግደል ይልቅ እንዲሞቱ መመኘት ቀላል ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ሰዎችን ከመግደል ይልቅ እንዲሞቱ መመኘት የበለጠ ቀላል ሆኖ አግኝቼዋለሁ።” ስትል አስፍራ ነበር ።
ታዲያ ፍርድ ቤት ፖሊስ ያቀረበለትን ማስረጃ ለሁለት ቀናት በማሰብ አዎ አንቺ በሁለተኛ ደረጃ ግድያ ወንጀለኛ ነሽ ብሏል ።
ክሪምፕተን በሕዝብ በተጨናነቀው ፍርድ ቤት ለተላለፈው ብያኔ ምንም ዓይነት ምላሽ ከመስጠት ተቆጥባለች ።
ቢሆንም ከጠበቆቿ አንዷ የሆነችው ሊሳ ማክስፊልድ የተወሰነው ውሳኔ ትክክል አይደለም ክሪምፕተን አዳላችሁት ነብሰ ገዳይ ሳትሆን ንጹ ሰው ናት ስትል ተከራክራለች ።ፖሊስ ጨምሮ ተጠርጣሪዋ ባሏ በሞተበት ዕለት በምግብ ቤቱ አቅራቢያ ያለ ትምህርት ቤት ውስጥ ተገኝታ እንደነበር ያስታውቀ ሲሆን ጠበቃዋ ግን እዛ የተገኘችው አዲስ ለምትጽፈው ጽሁፍ ግብዐት ለማሰባሰብ እንደሆነ ተናግራለች ።
ፍርድ ቤት የተከሳሽ ጠበቃ ያቀረበችውን ማስተባብያ ተቀብሎ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ሰቷል ። ነገር ግን ደራሲዋ አሁንም በ እስር ቤት ውስጥ ናት ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-05-30
