ሀገሬ ቲቪ

ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን

ከገቢና ወጪ ዝውውር ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ማዳን ተችሏል ተባለ፡፡ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር በባቡር የሚደረግ የገቢና ወጪ ዝውውር እንዲጨምር መደረጉ፣ ሸቀጦችን በኮንቴነር አሽጎ መላክ መቻሉ እና በሌሎችም በ9 ወራቱ ውስጥ ከ2.32 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ ማዳን ተችሏል ብሏል፡፡

ባልተደራጀ መለኩ ይጓጓዝ የነበረው ቡና በሀገር ውስጥ በኮንቴነር አሽጎ ወደ ወደብ ማጓጓዝ በመጀመሩ ወደ ውጪ ከተላከው ቡና 97ነጥብ7 ከመቶ በኮንቴነር ታሽገው የተላከ ሲሆን ይህም ቅሸባን በማስቀረትና የሚወስደውን የተራዘመ የጉዞ ጊዜ ጭምር ማሳጠር ተችሏል፡፡ሚንስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በቡና ኮንቴነራይዜሽን የተገኘው ስኬት በቅባትና በጥራጥሬ ምርቶች ላይ መድገም እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡የሞምባሳ/ሞያሌ ኮሪደርን በሙከራ ደረጃ በተያዘው ዓመት ወደ ስራ ማስገባት መቻሉ እንዲሁም የታጁራ ወደብ አገልግሎት መስጠት መጀሩ የወደብ አማራጮችን ከፍ እንዲል አድርጓል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-05-31