ሀገሬ ቲቪ

የቻይና የጦር አውሮፕላኖች ወደ ታይዋን

ታይዋን ቻይና 30 የጦር አውሮፕላኖችን ወደ አየር ክልሌ ልካለች ስትል ስሞታ አቀረበች።ይኽ ተግባር ከጥር ወር ወዲህ ከበድ ያለ ነው ተብሏል። የታይዋን የአየር ክልሌ በቻይና ተጥሷል ወቀሳ የተሰማው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ከታይዋን ጎን ቆመው ለቻይናን ማስጠንቀቂያ የታከለበት ማሳሰቢያ ከሰጡ በኋላ ነው።

የአሜሪካ ባለሥልጣናት ደሴቷን ታይዋን በጎበኙበት ወቅት ከሀገሪቱ ሹማምት ጋር በደህንነት ጉዳይ መምከራቸው ተወርቷል። ቻይና ታይዋንን የአካሌ ክፋይ ናት እንጂ ራሷን የቻለች ሀገር አይደለችም ባይ ናት። ይኽን ተከትሎ ታይዋንን በእጄ ማስገባቴ አይቀርም ማለቷ በቀጠናው ክፍተኛ ስጋት እና መረበሽ ፈጥሯል።

በአብርሃም በለጠ
2022-05-31