ከ11 እስከ 18 ዓመት እድሜ ካላቸው 10 ልጆች ዘጠኙ የኑሮ ውድነት እያስጨነቃቸው ስለመሆኑ ጥናት ጠቆመ። ዮርክሹሪ ቢውልዲንግ ሶሳይቲ የተሰኘ ተቋም ባጠናው ጥናት መሠረት በጥናቱ ከተካተቱት ልጆች ከአምስቱ ሶስቱ ስለወላጆቻቸው አስፈላጊ ነገሮችን ለማሟላት በቂ ገንዘብ አለመኖር ይጨነቃሉ።
በጥናቱ ከተሳተፉት አንድ ሺህ ከ11 እስከ 18 ዓመት የሆናቸው የእንግሊዝ ልጆች ከ750 በላይ የሚሆኑት ቤተሰቦቻቸው በኑሮ ውድነቱ ሳቢያ ቁጠባን የማቆም ሀሳብ አላቸው ተብሏል። ከልጆቹ ወላጆች 55 በመቶ ያክሉ የምግብ እና የኃይል ወጪን ለመቀነስ እየሞከሩም ነው ተብሏል። 27 በመቶ የሚሆኑት ወላጆች ደግሞ እንደ ነዳጅ ያሉ አስፈላጊ ወጪዎችን አቋርጠዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-05-31
