እነዚ ሰዎች ይሄን በረራ የተሳካ ለማድረግ የ ድጋፍ እጃችሁን ዘርጉልን ሲሉ ለበርካታ ተቋማት ጥያቄ አቀረቡ ።
ነገር ግን ከፓስፊክ ውቅያኖስ ተሻግሮ ለመብረር ማሰብ ሞኝነትና ሊሳካ የማይችል ነው በማለት ብዙዎች እሽታን ነፈግዋቸው
ለስራው መሳካት ደጋፊ አካላትን ባሰቡት ልክ ባለማግኘታቸው ስሚዝ ፓስፊክ ውቂያኖስን አቋርጦ የመብረር ሞራሉ እየተዳከመ መጣ።
ታዲያ ይህን ጉዳይ የሰሙት የወቅቱ የአሜሪካ ሚሊየነር የነበሩት ካፕት ጂ ለስሚዝ አውሮፕላኑን ገዝተው በመስጠት እንዲሁም ተጨማሪ ገንዘቦችን በመደጎም ሥራው እንዲቀጥል አገዟቸው ።
ከብዙ ቅድመ ጥናቶች በሁላም ስሚዝና አጋሮቹ ካሉበት 8000 ማይል አቋርጠው አውስትራሊያ ለማረፍ የመጀመሪያ ቀን በረራቸውን አደረጉ ። በመጀመሪያ ቀን 2408 ኪሎ ሜትር ያህል በመጓዝ ማረፊያቸውንም ሃዋይ አደረጉ ።
በቀጥዩም ቀን 3400 ኪሎ ሜትር የተጓዙ ሲሆን በሶስተኛው ቀን 1880 ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ ታላቁን ፓስፊክ ውቅያኖስ አቋርጠው አውስትራሊያ በመግባት በብዙዎች ልብ ውስጥ የማይታሰብ የነበረውን ድርጊት ስሚዝና ጓደኞቹ አሳኩ ።
የዛሬው ዕለቱን ከታሪካችን በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሜይ 31, 1928 ማለትም ከዛሬ 90 አመታት በፊት አንድ አብራሪ በካሊፎርኒያ ከሚገኘው የኦክላንድ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ የማይሳካ የሚመስለውን የፓስፊክ ውቂያኖስን በ አየር በማለፍ ወደ አውስትራሊያ የገቡበትን ዕለት ይዳስሳል ።
በዮሴፍ ከበደ
2022-05-31
