ሀገሬ ቲቪ

የገቢዎች ሚኒስቴር እርምጃ

በሽያጭ መመዝገቢያ መሳሪያዎች ከ32 ቢሊዮን ብር በላይ ሀሰተኛ ግብይት መፈፀማቸው በምርመራ ተረጋገጠ፡፡ ህገ-ወጥ ድርጅቶች ሲጠቀሙባቸው በነበሩ የካሽሬጂስተር ማሽኖች ነው ሀሰተኛ ግብይት የተፈጸመው ፡፡ የገቢዎች ሚኒስቴር ከሰሞኑ 63 ህገ-ወጥ ድርጅቶች እና ለህገ-ወጥ ዓላማ ሲውሉ የነበሩ 20 የሽያጭ መመዘገቢያ መሳሪያዎች መያዙን ይፋ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ በተያያዘ ደረሰኝ የማይቆርጡ ድርጅቶች ላይ በተደረገ ክትትል 199 ሰዎች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በታክስ አስተዳደር አዋጅ 983/2008 አንቀፅ 108 ድንጋጌ መሠረት ብር 8ሚሊዮን 150ሺሕ አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጣልባቸው ተወስኗል፡፡ ህብረተሰቡ ሀሰተኛ ደረሰኝ የሚያሰራጩና በግብይት ወቅት አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥመው የታክስ ማዕከልና የፀጥታ አካላትን እንዲያሳውቅ የገቢዎች ሚኒስቴር ጥሪ አቅርቧል፡፡

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-06