ሀገሬ ቲቪ

የአየር መንገዱ አዲስ የበረራ መስመር

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቶጎ ሎሜ በኩል ወደ ዋሽንግተን ዲሲ አዲስ በረራ ዛሬ ጀመረ፡፡

ከዚህ ቀደም አየር መንገዱ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በአየርላንድ ደብሊን አድርጎ በረራ ያደርግ ነበር ያሉት የኢትዮጵያ አየርመንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሠው የዛሬው አዲስ የበረራ መስመር አፍሪካን ከአሜሪካ ለማገናኘት ይረዳል፡፡

አየር መንገዱ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ ከፈረንጆቹ 1998 ጀምሮ ይበራል፡፡ በሎሜ በኩል የሚደረገው በረራ በቦይንግ 787 አውሮፕላን እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ 116 ዓለም አቀፍ እና 23 የሀገር ውስጥ መዳረሻዎች እንዳሉት መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች ቁጥር በአፍሪካ 62፣ በአውሮፓ፣ በሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ 22 እንዲሁም በገልፍ፣ መካከለኛው ምስራቅ እና እስያ 26 ከተሞች መድረሱ ተመላክቷል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-01