ሀገሬ ቲቪ

‹‹ተስፋ ለአፍሪካ››

የአየር ንብረት ለውጥ መላመድ የአፍሪካን የግብርና ምርታማነት ሊከፍት እንደሚችል ተስፋ እየሰጠ ነው፡፡

ግብርና እስካሁን ድረስ በአፍሪካ ውስጥ በጣም አስፈላጊው የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ነው፡፡ከአህጉሪቱ ሁለት ሦስተኛ ለሚሆነው ሰራተኛ የስራ እድል የሚሰጥ ሲሆን ለእያንዳንዱ ሀገር በአማካይ ከ30 እስከ 60 በመቶ የሚሆነውን አጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ወይንም ጂዲፒ እና 30 በመቶውን የወጪ ንግድ ይሸፍናል፡፡

ይህ አሃዝ ግን እጅግ በጣም ጥቂት እንደሆነ የሚናገረው ዓለም አቀፉ የምግብ እና ግብርና ድርጅት (ፋኦ) አህጉሪቱ ሙሉ አቅሟን ብትጠቀም ከዚህ በላቀ ሁኔታ ከሁለት እስከ ሦስት እጥፍ የሚበልጥ እህል፣ የአትክልት ሰብሎች እና የእንስሳት እርባታ እና ሌሎችም ማምረት እንደምትችል ይተነብያል ፡፡

የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፋይናንስ ሚኒስትር ድህነት እና ወሳኝ ግብአት አቅርቦት አናሳ መሆን እንደ ኃይል እና ውሃ ያለማግኘት አህጉሪቱ ያላትን እምቅ አቅም እንዳታሳካ ትልቅ ሚና እንዳላቸው ያስረዳሉ፡፡ ሚኒስትሩ ኒኮላስ ካዛዲ ካዲማ ሲጨምሩ “በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ካለን 155 ሚሊዮን ደን ውስጥ በዓመት 1 ሚሊዮን እናጣለን እና በጣም ብዙ ነው፡፡ የአካባቢ ጥበቃ ከምንም በላይ የልማት ጥያቄ ነው፡፡”

የዓለምአቀፍ የመላመድ ማዕከል ዋና ስራ አስፈፃሚ ፓትሪክ ቬርኮኢጅን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ የግብርናውን ዘርፍ ምርታማነት ወደ ኋላ እየገታ ነው ብለው ያምናሉ፡፡ በአህጉሪቱ የሙቀት መጠኑ እየጨመረ በመምጣቱ እስከ 30 በመቶ የሚሆነው የበቆሎ ምርት ይጠፋል ያለውን ትንበያ በመጥቀስ፡፡

“ለአብነትም ድርቅን የሚቋቋሙ ዘሮችን ማስተዋወቅ አለብን የአየር ንብረት ድንገተኛ አደጋን የሚቋቋሙ ዛፎችን መትከል እንደዚሁ ፣ አግሮ ደንን መጠቀም እና ምርቶችን ለዓላማ ተስማሚ በማድረግ ዓለም አቀፍ ገበያዎችን ማግኘት አለብን፡፡›” ሲሉ ምክራቸውን ይለግሳሉ፡፡

የዓለምአቀፍ የመላመድ ማዕከል እና የአፍሪካ ልማት ባንክ በ2025 በአፍሪካ 25 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ቆርጠዋል፡፡ከገንዘቡ ውስጥ ግማሹን ለ30 ሚሊዮን አነስተኛ ማሳ አርሶ አደሮች በአፍሪካ መላመድ መርሃ ግብር በመመደብ፡፡

ይህን የማላመድ መርሃ ግብር ከአፍሪካ ልማት ባንክ ባልደረባ እና የግብርና ፖሊሲ ኢኮኖሚስት ፊሊፕ ቦሄን እንደተናገሩት የጥበቃ አሠራሮችን መውሰዱ አፈሩን በመንከባከብ ላይ ያለውን ባዮማስ በማሻሻል ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡

“የእርሻ ጥበቃን ለማስተዋወቅ አንዱና ዋነኛው የችግኝ ተከላ ተግባር ነው፡፡ አርሶ አደሮችን በኢኮኖሚያዊ ዛፎች በመደገፍ የበለጠ ምርት እንዲያመርቱ እናደርጋለን፡፡”

ባንኩ ከጋና መንግሥት ጋር በመተባበር የኢንቨስትመንት መርሃ ግብር በመተግበር የበቆሎ፣ አኩሪ አተር፣ ሩዝ እና ሌሎች የምግብ ሰብሎችን ምርት በከፍተኛ ደረጃ ያሳደገ መሆኑ ተገልጿል፡፡የጋና የምግብ እና ግብርና ሚኒስቴር ፌሊክስ ዳሪማኒ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡

“በሄክታር ከሁለት ሜትሪክ ቶን በታች ይገዙ የነበሩ አርሶ አደሮች በአሁኑ ወቅት በሄክታር 6.25 ሜትሪክ ቶን በቆሎ እና በአኩሪ አተር 2.5 ሜትሪክ ቶን እየመዘገቡ ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ በጋና ግብርናውን የሚደግፉ ከ350 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ የተለያዩ የምግብ ሸቀጦችን አምርተናል፡፡”

የኢንቨስትመንት ፕሮጀክቱ ከውጭ የሚገቡ የእንስሳትን ፕሮቲን ለመቀነስ፣ በጋና የምግብ ዋስትናን ለማሻሻል እና የዶሮ እርባታ ኢንዱስትሪን ለማስፋት ያለመ ነው ሲሉ ፊሊፕ ቦሄን ገልጸዋል፡፡

“ፕሬዝዳንቱ ከ120 ሺሕ ሄክታር በላይ በቆሎ እና አኩሪ አተር እና ሩዝ ከ300 ሺሕ ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብ እቃዎችን እንዲያመርቱ ድጋፍ አድርጓል፡፡”

በሰሜን ጋና የፕሮጀክቱን ስኬት ተከትሎ ባንኩ ይህን ሞዴል በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ናይጄሪያ፣ ዛምቢያ፣ አይቮሪ ኮስት፣ ኡጋንዳ እና ኬንያን በመድገም ላይ ይገኛል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-01