ሀገሬ ቲቪ

ከ50 ዓመታት በኋላ ወደ አስትሮይድ

ሰዎች ከ2071 እስከ 2087 ባሉት ዓመታት በአስትሮይድ ላይ ሊያርፉ ይችላሉ ሲል አንድ ጥናት ጠቆመ። የጠፈር ተመራማሪ ሀገራት ተልእኮአቸውን ከማርስ ባሻገር ወደ አስትሮይድ ማማተር አለባቸው ሲል አስትሮኖምይ ዶት ኮም ጽፏል።

የሮኬት መሐንዲሶች እንደተናገሩት በ2038 የሰው ልጅ ማርስ ከደረሰ የመጀመርያው የሰው ልጅ የጠፈር ተልዕኮ ወደ አስትሮይድ ቀበቶ በ50 ዓመታት ውስጥ ሊካሄድ ይችላል ብለዋል። አስትሮይድስ በፀሐይ ዙሪያ የሚዞሩ ትናንሽ ዓለታማ ነገሮች መሆናቸው ይታወቃል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-06-01