ቻይና ከሩስያ የምታደርገው የነዳጅ ዘይት እና ጋዝ ግዥ ድጋፍ አሜሪካን ሊያስቆጣት እንደሚችል ተመላከተ።
የአውሮፓ ህብረት ዋና የሩስያ ነዳጅ ገዥ ሃገራት ከሩስያ ያላቸውን የነዳጅ ግዥ ለማቋረጥ ተስማምተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስምምነት ላይ ባይደርስም አሜሪካ፣ አውሮፓ እና ጃፓን ሞስኮን ከገበያቸው እና ከባንክ ስርዓታቸው ሲያስወጧት ቻይና ድርጊቱን ተቃውማለች።
ምዕራባውያኑ በሩስያ የሃይል አቅርቦት ላይ የጣሉት ማእቀብ ቻይና፣ ህንድም ሆነች ሌላ ሃገር ከሩስያ ነዳጅ እንዳይገዙ አይከለክልም።
እንደ ባይደን ገለጻ ግን ሞስኮ ከማእቀቡ እንድታመልጥ ቤጂንግ የምትረዳት ከሆነ የቻይና ድርጅቶች የማዕቀብ ሰለባ ይሆናሉ ብለዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-06-01
