ቡና መጠጣት ለሞት የመጋለጥ እድላችንን ሊቀንስ ይችላል ሲል በዓለም ላይ ትልቁ የሆነው የባዮሜዲካል ምርምር ኤጀንሲ. NIH በድህረ ገጹ ላይ ይፋ ያደረገው ጥናት ጠቆመ።
ጥናቱ ቡና ውስጥ ስኳር ቢኖር እንኳን መጠኑ ዝቅተኛ ከሆነ ለሞት የመጋለጥ እድላቸንን ይቀንሳል ይላል ።
በጥናቱ ቡና የሚጠጡ ሰዎች የመሞት እድላቸው ከ16 እስከ 21 በመቶ ቡና ካልጠጡት ሰዎች ያነሰ መሆኑን ውጤቱ ያሳያል።
ቡና በስኳር የሚጠጡ ሰዎች ደግሞ ከ 29 እስከ 31 በመቶ ቡና ካልጠጡት ሰዎች የመሞት እድላቸው አነስተኛ ነው።
ቡና ጠጪዎች በልብ ሕመም፣ በመተንፈሻ አካላት በሽታ፣ በስኳር ና በበሽታ የመሞት እድላቸው አነስተኛ ነው ፤በካንሰር ላይ ያለውን ተጽእኖ ቀጣይ እንደማጠና እወቁልኝ ብሏል ተቋሙ።
ዶ/ር ኔል ፍሪድማን እና ባልደረቦቹ ባደረጉት ጥናት 400ሺሕ አሜሪካውያን ወንዶች እና ሴቶች ተሳትፈዋል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-01
