የገቢዎች ሚኒስቴር የታክስ ክፍያ በኤሌክትሮኒክስ ዘዴ ለማሰባሰብና ግብር ከፋዮች በበበይነ መረብ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ከኦሮሚያ፣ ወጋገንና ዘመን ባንክ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።
ሚኒስቴሩ ንግድ ባንክን ጨምሮ ከአራት ባንኮች ጋር እየሰራ መሆኑ ተሰምቷል።
የታክስ አስተዳደር ስርዓቱን ዓለም በደረሰበት ቴክኖሎጂ ለመደገፍ መስሪያ ቤቱ አልሟል።
ግብር ከፋዮች ማንኛውንም አገልግሎት ካሉበት ቦታ ሆነው እንዲጠቀሙ ደራሽ የተሰኘ መተግበሪያ አልምቶ ወደ ሥራ መግባቱም ታውቋል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-01
