ሀገሬ ቲቪ

በ39 ሚሊየን ብር የተገነባው የሮቤ ኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኢፈ ቦሩ ፕሮጄክት ስር የተገነባው የሮቤ ኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡ በትምህርት ቤቱ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡ ለትምህርት ቤቱ ግንባታ 39 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን፥ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ 700 ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ተብሏል፡፡ መማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ ቤተ መጽሐፍት፣ ቤተ ሙከራ እና የኮምፒውተር ላቦራቶሪዎችን ያካተተ ነው፡፡

በሀገሬ ቴቪ
2021-06-03