ሀገሬ ቲቪ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጥገና ስራ

የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመሮችን በመጠገን ከስርጭት መስመሮች ጋር የማገናኘት ሥራ እየተሰራ መሆኑ ተሰማ፡፡ በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ግጭት የሕወሓት ቡድን በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ የደረሰውን ጉዳት ነው ቢሮው እየተጠገነ ያለው፡፡ ቡድኑ ተቆጣጥሯቸው በነበሩ አካባቢዎች በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጥገና ባለሙያዎች በተንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች በጥይት ተመተው የመበጣጠስና የምሰሶዎችን መውደቅ መመልከታቸው ተነግሯል፡፡ የጥገና ሥራ ከተጀመረባቸው አካባቢዎች መካከል ከለገዳዲ- ደብረብርሃን - ሸዋ ሮቢት - ኮምቦልቻ ይገኙበታል፡፡ እስከ ሸዋ ሮቢት ያለው መስመር ደግሞ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወሳል። ከ ቡድኑ ነፃ ከወጡት አካባቢዎች መካከል ከሸዋ ሮቢት እስከ ከሚሴ ድረስ ያለውን መስመር በቀጣዮቹ ሁለት ቀናት ይጠገናል ተብሏል፡፡ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስርጭት መስመሮች ጋር በማገናኘት አካባቢዎቹ ኤሌክትሪክ እንዲያገኙ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

በሀገሬ ቲቪ
2021-12-06