ሀገሬ ቲቪ

ለጉዳተኞች ሀላፊነት በመስጠት ህገወጥ አሰራርን ማስቀረት

የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪና የሰው ሀብት ቢሮ በከተማችን ከአገልግሎት አሰጣጥ : ከብልሹ አሰራሮችና ከሌብነት ጋር በተያያዘ በተገልጋዮች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ አካል ጉዳተኛ ሰራተኞችን አመራር ቦታ ላይ ማስቀመጥ የተሻለ ሆኖ አጊንቼዋለሁ ብሏል።

ቢሮው በአንዳንድ የመንግስት ስራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ አካል ጉዳተኛ ሰራተኞችን ከፍ ወዳለ የአመራር ቦታ ለማስቀመጥ በማሰብ የ 3 ቀናት ስልጠና ዛሬ ያስጀመረ ሲሆን ።አካል ጉዳተኞችን በከፍተኛ አመራር ቦታ ላይ ማስቀመጡ ለማህበረሰቡ እፎይታን የሚሰጥ መሆኑን የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኅላፊ አቶ ሀይሉ ሉሌ ነግረውናል።

አካል ጉዳተኞችን ወደ አመራር ቦታ የማምጣት እቅድ ከተጀመረ በኋላ በብዙ ክፍለ ከተሞች የማህበረሰቡን እንግልት እንደቀነሰና ከማህበረሰቡም በጎ ምላሽ እንደተገኘ አቶ ሀይሉ ይናገራሉ።አካል ጉዳተኞችን ወደ ተሻለ ሀላፊነት ማምጣቱ የሚበረታታ ቢሆንም በተለያዩ ቢሮዎች ያሉ መሰረተ ልማቶች ለአካል ጉዳተኞች ምቹ አይደሉም።

ሀላፊው በዚህ ጉዳይ ላይ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ይህን መልሰዋል። ማህበረሰባችን ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠው እንከብካቤ የሚበረታታ ቢሆንም በአንዳንድ ቦታዎች ቅድሚያ አለመስጠት ይስተዋላል። ዛሬ በስልጠናው ላይ የተገኙት ሰልጣኞችም እኛ በየተኛውም ቦታ ሀላፊነት ወስደን መስራት እንችላለን እድል አትንፈጉን ሲሉ መልዕክታቸውን አሰምተዋል።

በዮሴፍ ከበደ
2022-06-01