የሚኒስተሮች ግብረ ሃይል ለአውሮፓ ሃገራት አምባሳደሮች በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል ከግጭቱ ጋር በተያያዘ የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ መንግስት ስለሰራቸው ስራዎች ገለጻ ተደረገ።
በመግለጫው የግብረ ሃይሉ ዋና ጸሃፊ የሆኑት ዶ/ር ታደሰ ካሳ ዘጠኝ አጣሪ ቡድኖች ተመድበው በአፋር እና አማራ ክልል ዘጠኝ ቦታዎች ከሺህ የሚቆጠሩ የአይን እማኞች ምስክርነት እና ገላጭ መረጃዎች መሰብሰባቸውን ገልጸዋል።
ለአጣሪ ቡድኑ ስለጾታ ተኮር ጥቃቶች አለም አቀፍ መስፈርቶችን በጠበቀ መልኩ ከአለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር ስልጠና ስለመሰጠቱም ዶ/ር ታደሰ ተናግረዋል።
በአብርሃም በለጠ
2022-06-02
