የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ባለፉት 9 ወራት ከ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ተጎጂዎች ሰብዓዊ እርዳታ ሰጥቻለሁ አለ።
ባለፉት 3 ወራት በተከሰቱ ሰው ሰራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ለተጎዱ 20 ሺሕ ወገኖች የምግብ እርዳታ እንዲሁም 30 ሺሕ ለሚሆኑት ደግሞ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሰብዓዊ ድጋፎች አድርጓል።
ማኅበሩ 15 ሺሕ ለሚሆኑ ልዩ ልዩ የመድኃኒት እና ምግብ ነክ እርዳታዎችን ማድረጉንም አስታውቀዋል።
የሞባይል አጭር የጽሁፍ መልዕክት መላኪያን በመጠቀም ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አግኝቻለው ብሏል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-02
