ዩጋንዳ ሙሉ ለሙሉ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት በመጠቀም የመጀመሪያዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ሆናለች።
የአዲሱን ትውልድ ፓስፖርት ወይንም የኢ ፓስፖርትን ያልተመዘገቡ ዩጋንዳውያን ከዋና ከተማዋ ኢንቴቤ መውጣት አይችሉም ተብሏል።
በአውሮፓውያኑ መጋቢት 2016 ሀገሪቷ የኤሌክትሮኒክስ ፓስፖርት ለመጠቀም በታንዛኒያ ስምምነት ካደረጉ ሀገራት ተርታ ትመደባለች።
ኬንያ ባለፈው ዓመት ታኅሣሥ ለማስጀመር ብታቅድም ሳይሳካላት ቀርቷል።
የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ(ኢ.ኤ.ሲ) ዋና ጸሃፊ ፒተር ማቱኪ በቅርቡ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት መስፈርቶችን ተግባራዊ ያላደረጉ አባላት በፍጥነት ተግባራዊ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
60 ሀገራት የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርቶችን ለመጠቀም ፍላጎት ማሳየታቸውን ቢዝነስ ዴይሊ ዘግቧል።
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-02
