በኬኒያ የኮቪድ 19 ክትባትን ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ዜጎች ቁጥር ከ2 ነጥብ 9 ሚሊዮን ማለፉ ተነገረ፡፡ ኬኒያ ማንኛውም የሀገሪቱ ዜጋ ክትባቱን እንዲወስዱ ጥሪ ስታቀርብ ብትቆይም ያሰበችውን ያህል ዜጋ መከተብ አለመቻሏ የሚታወስ ነው፡፡ ይህን በዜጎቿ ክትባቱን ችላ የማለት ችግር ለመቅረፍ ታዲያ አዲስ መመሪያን እያዘጋጀች መሆኑን ከሳምንታት በፊት አስታውቃ ነበር፡፡ መመሪያው በዋናነት ክትባቱን የማይወስዱ ዜጎች ማንኛውም የህዝብ መጓጓዣ እንዳይጠቀሙና አገልግሎት ፍለጋ ወደ መንግስት መሥሪያ ቤት ድርሽ እንዳይሉ የሚል ነው፡፡ አሁን ላይ ታዲያ ኬኒያ ክትባቱን የሚወስዱ ዜጎች ቁጥር እንዳሰብኩት እየጨመረልኝ ነው ስትል አስታውቃለች፡፡ ከ ሁለት ሚሊየን በላይ ዜጎች ሙሉ ለሙሉ ሲከተቡ ከአራት ሚሊዮን በላይ ሰዎች ደግሞ በከፊል ክትባቱን ወስደዋል፡፡ በሀገሪቱ እየተሰራጩ ያሉት ክትባቶች በቻይና የተመረተ ሲኖፋርም፣ አስትራዜኔካ፣ ፒፊዘር እና ሞደሬና ይገኙበታል።
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-06
