በጎርጎሮሲያኑ የዘመን ቀመር በ1989 በቻይና ዋና ከተማ ቤጂንግ እጅግ አስደንጋጭ ክስተት ታየ። ክስተቱ የቻይና መንግሥት በሕዝቡ ላይ የፈጸመው አሰቃቂ ግድያ እና እልቂት ነበር።
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና ሠራተኞች መንግሥት እያካሔደ ያለው የፖለቲካ እና ምጣኔሀብታዊ አመራር እየተዋጠልን አይደለም ሲሉ መንግሥት ላይ አጉረመረሙ። ቻይና 1980ቹ ከፍተኛ ምጣኔሀብታዊ ለውጥ ያሳየችበት ዓመት ነው።
የዚያኔው የቻይና መሪ ዴንግ ሺኦፒንግ እና የኮሚኒስት ፓርቲአቸው ለአንዳንድ የግል ኩባንያዎችንና የውጭ ኢንቨስትመንቶች ፍቃድ የሠጠበት ዓመት ነበር።
በወቅቱ ቻይና ጥሩ የምጣኔ ሀብት ዕድገት እና ነጻነት ብታሳይም፤ ኢኮኖሚው ለሕዝቡ የሥራ ዕድል ጥሩ መደላድል ቢፈጥርም አብሮ ሲጓዝ የነበረው የዋጋ ግሽበት እና የሀገሬው ሹማምንት ዐይን ያወጣ የሙስና ወንጀል ከባድ ተቃውሞ እና የሕዝብ አመጽን አስነሳ።
የኮሚኒስት ፓርቲው ፈጣን ለውጥ በሚደግፉና እና ጥብቅ የመንግስት ቁጥጥርን ለማጠንከር በሚፈልጉ አባላት መካከል ሊከፋፈል ቻለ።
በዚህ ትርምስምስ ውስጥ ታዲያ ተማሪዎች ለአመጽ አደባባይ መውጣት ጀመሩ። አመጹን ከቻይና ውጪ በሌሎች ሀገር የሚኖሩ ዜጎችም የምንጋራው ነው በአካል ከናንተ ጋር ባንሆንም በትግል መንፈስ ከናንተው ጋር ነን ሲሉ ተቃውሞ አድራጊ ተማሪዎችን ማበረታታት ያዙ።
እንደ ጎርጎሮሲያኑ 1980 ጅምሮ ከፍ ዝቅ፣ ሞቅ በረድ ሲል የነበረው የተማሪዎች ተቃውሞ 1989 በዛሬው ዕለት ከምንጊዜውም በላይ ተስፋፍቶ እና ተጋግሎ ቀጠለ።
ፖለቲካዊም ሆነ ምጣኔህብታዊ ለውጥ እንዲመጣ ትግል ሲያድርጉ የነበሩት ፖለቲከኛው ሁያኦባንግ መምታቸው ደግሞ ተማሪዎች ትግላቸውን እንዲያጠነክሩ ምክንያት ሆነ።
በቀብራቸው ሥነስርዓት ላይም በአስር ሺዎ የሚቆጠሩ ዜጎች ተሰብስበው የበለጠ የመናገር ነፃነት እና ሳንሱር እንዲቀንስ ጠይቀዋል።
በቀጣዮቹ ሳምንታት ውስጥም ተቃዋሚዎች በቤጂንግ ቲያናንመን አደባባይ ተሰብስበው ተቃውሞአቸውን ማሰማት ጀመሩ። በዚኽ አደባባይ የተገኘው እና የወቅቱን መንግሥት የተቃወመው ሕዝብ ቁጥር እስከ 1 ሚሊዮን እንደሚገመት ወቅቱን የሚያወሱ ጽሑፎች ይገልጻሉ።
ይኽን ጊዜ ነበር አስከፊ የተባለው የመንግሥት የእርማጃ እጅ በሕዝቡ ላይ ያረፈው። የኮሚኒስት ፓርቲው አመራሮች ምን ዓይነት ምላሽ መሥጠት እንዳለባቸው ከስምምነት መድረስ አልቻሉም ነበር ገሚሱ እርምጃ እንውሰድ ሲል ገሚሱ የለም ጠንከር ያለ እርምጃ ወስደን ሰልፉን እንበትነው ሲሉ ተሟገቱ።
በዚኽም ጠንከር ያለ እርምጃ እንውሰድ ያሉት አባላት አሸናፊ ኾኑ። ባቀዱት መሰረትም በአውሮፓውያኑ ጁን 3 እና ጁን4 ማለትም በዛሬው ቀን እና በተከታዩ ቀን ቲያናንመን አደባባይ በተሠበሰቡ ዜጎች ላይ በታንክ የታገዘ ተኩስ በመክፈት
ምን ያኽል ሰዎች እንደተገደሉ በእርግጠኝነት የሚያውቅ የለም። ነገር ግን መንግሥት የሞቱት ንጹኃን እስከሁለት መቶ እንደሚደርሱ እና ከአስር በላይ የጸጥታ አባላት እንደሞቱ ተነግሮ ነበር። ይኽ አሀዝ ግን የተሳሳተ ነው የሟቾች ቁጥር በሺ የሚቆጠር ነው የሚሉ በርካቶች ናቸው። ከእንግሊዝ ሀገር የወጣ አንድ ዶክመንት እንደሚያሳየው ከሆነ ግን 10,000 ንጹሀን ሰዎች መሞታቸውን ተናግረዋል ።
በሙሉጌታ በላይ
2022-06-03
