መንግሥት የ2015 በጀት ብር 786ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር ሆኖ እንዲጸድቅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
የሚንስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሔደው 9ኛ መደበኛ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በ2015 የፌደራል መንግሥት በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
ለ2015 በጀት ዓመት ለመደበኛ ወጪ ብር 347ነጥብ12 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪ ብር 218ነጥብ11 ቢሊዮን እንዲሁም ለክልል መንግሥታት ድጋፍ ብር 209 ነጥብ 38 ቢሊዮን እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ብር 12 ቢሊዮን የተያዘ ሲኾን አጠቃላይ የፌደራል መንግሥት የ2015 በጀት ብር 786.61 ቢሊዮን ሆኖ ቀርቧል፡፡
የቀጣዩ ዓመት በጀት ከ2014 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የብር 111ነጥብ 94 ቢሊዮን ወይም የ16ነጥብ 59 በመቶ እድገት አለው ተብሏል፡፡
በሙሉጌታ በላይ
2022-06-03
