የዓለም ጤና ድርጅት በአፍሪካ በ2022 የኮቪድ-19 የሚሞቱ ዜጎች ቁጥር በ94 በመቶ ይቀንሳል አለ፡፡
በዚህ ሳምንት በሳይንሳዊ ጆርናል ላንሴት ግሎባል ሄልዝ የታተመው ትንታኔ እንደሚያሳየው በክልሉ በ2021
ትክክለኛው የሟቾች ቁጥር 350 ሺሕ ነው፡፡በአንጻራዊነት በ2022 መገባደጃ ላይ የሞቾች ቁጥር 23 ሺሕ ሊደርስ እንደሚችል ገልጿል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ዶ/ር ማትሺዲሶ ሞኢቲ እንዳሉት “ባለፈው ዓመት በየቀኑ በአማካይ 970 ሰዎችን አጥተናል፤ ይህ እጅግ አሰቃቂ አደጋ ነው፡፡”
ድርጅቱ የቅርብ ጊዜ ትንታኔ እንደሚያመለክተው በአፍሪካ ክልል የሚገመተው ሞት በ2022 ወደ 60 በቀን ይቀንሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ይሁን እንጂ ሥራው ገና አልተጠናቀቀም ብለዋል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-03
