የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች 116 ሺሕ 27 አዲስ ተለዋዋጭ ኮከቦችን አግኝተዋል፡፡
የኦል-ስካይ አውቶሜትድ የዳሰሳ ጥናት በመጠቀም እንዲሁም ሌሎች በርካታ ጥናቶችን በመጠቀም የስነ ፈለክ ተመራማሪዎች 378ሺሕ 861 ተለዋዋጭ ኮከቦችን ለይተው አውቀዋል፤ ከነዚህም 262ሺሕ 834ቱ የታወቁ ተለዋዋጮች እንዲሁም 116 ሺሕ 27 አዳዲስ ግኝቶች ናቸው፡፡
በኦሃዮ ዩኒቨርሲቲ የስነ ፈለክ ጥናት ክፍል ውስጥ የሥነ ፈለክ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ኮሊን ክሪስቲ እንደገለጹት ካጠኗቸው 1.5 ሚሊዮን ኮከቦች ውስጥ 378ሺሕ 861 ያህሉ እውነተኛ ተለዋዋጭ ኮከቦች ሆነዋል፡፡
ከግማሽ በላይ የሚሆኑት በሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ዘንድ ይታወቃሉ ብለዋል፡፡
ውጤቶቹ በሮያል አስትሮኖሚካል ሶሳይቲ ወርሃዊ ህትመቶች ላይ ይፋ እንደሚደረግ ሳይ ኒውስ ዘግቧል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-03
