ሀገሬ ቲቪ

የቻይናና ታይዋን ፍጥጫ

ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማግስት በቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ እና በናሽናሊስት የመንግሥት ኃይሎች መካከል ጦርነት እና የኮሚኒስት ኃይሉ ቤጂንግን መቆጣጠር መነሾነት ተሸናፊው ኃይል ታይዋን መሽጎ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1949 ጀምሮ ራሷ ታይዋንን ማስተዳደር ጀመረ።

ምንም እንኳን የቻይና ሕገ መንግሥት አሁንም ድረስ እንደ ቻይና አካል አድርጎ የሚቆጥራት ቢሆንም ከዋናው የቻይና አካል 160 ኪሎ ሜትሮች የምትርቀዋ ደሴት ራሴን የቻልኩ ሉዐላዊት ነኝ የምትል ከእርሷም አልፎ ቫቲካንን ሳይጨምር 13 ሀገራት እውቅና የሰጧት ግዛት ሆና ትገኛለች።ታይዋን ታዲያ ሉዐላዊ ነኝ ትበል እኚ ቻይናውያኑ እውቅና ካለመስጠታቸው በላይ አሁን በስልጣን ላይ ያሉት የቻይና ፕሬዝዳንት ሺ ዢን ፒንግ ታይዋንን መልሶ የቻይና አካል ለማድረግ ኃይል መጠቀም አማራጭ ሊሆን እንደሚችል ሀገራቸውም እርሳቸውም እነደሚያምኑ ይናገራሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ ታይዋን የራሷን ሕገ-መንግሥት እና በሕዝብ የተመረጠ መንግሥትም አላት።ለታይዋን ጠንካራ አጋርነቷን የምታሳየው አሜሪካም ብትሆነ ከታይዋን ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የላትም። የጦር መሳሪያዎችን ግን ለታይዋን ትቸበችባለች።

አሜሪካ ለታይዋን የጦር መሳሪያ የምትሸጠው ታይዋን እራሷን እንድትከላከል የመርዳት ኃላፊነት ስላለብኝ ነው ብላ ታምናለች።

ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በጃፓን እና በደቡብ ኮሪያ ባደረጉት የመጀመሪያ የእስያ ጉብኝታቸው በጎርጎሮሳውያኑ ግንቦት 23 ቻይናንና ታይዋንንን የተመለከተ ንግግር አድረገው ነበር ።

“አሜሪካ ቀደም ሲል አሻሚ የሚባለውን “አንድ ቻይና” የተሰኘውን ፖሊሲ ለመደገፍ ቃል ገብታ ነበር፤ ይህ ማለት ግን ቤጂንግ ታይዋንን ለመቆጣጠር ስልጣን አላት ማለት አይደለም ።” ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን

ቻይና በኃይል ታይዋንን ለመውረር ከሞከረች በወታደራዊ መንገድ አሜሪካ ጣልቃ እንደምትገባ ማስታወቃቸው ይታወሳል። ብዙዎች የባይደን ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ በዋሽንግተን ነግሶ የቆየውን አሻሚውን ፖሊሲ የሻረ ነው ብለዋል።

ባይደን “የሩስያ የዩክሬን ጦርነት” ና “የቻይና ታይዋንን ጦርነት” በማነጻጻር ቻይን እንደ ሩሲያ ሁሉ ለድርጊቷ የረዥም ጊዜ ዋጋ እንደምትከፍል አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

አሜሪካ ታይዋንን ከቻይና ለመከላከል ዩክሬን ከሩሲያ ጋር በምታደርገው ውጊያ ከነበረው የበለጠ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ ትወስዳለች ተብሎም ተወርቷል።

የጃፓኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ፉሚዮ ኪሺዳ እና የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደን ቻይናን እንዴት እንከላከል በሚል ርዕሰ ጉዳይ ዙርያም ሳይመክሩ እንዳለቀሩ አርቲ ጽፏል፡፡

የትራምፕ አስተዳደር የቀድሞ የመከላከያ ባለስልጣን እንዳሉት አሜሪካ ታይዋንን ለመከላከል እንደ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ ካሉ አጋሮቿ መስራት ይጠበቅባታል።

በአሜሪካ የጦር ኮሌጅ “የተሰበረ ጎጆ፡ ቻይና ታይዋንን ከመውረር መከላከል” በሚል በያሬድ ማኪኒ እና ፒተር ሃሪስ ለታይዋን መከላከያ ስትራቴጂ ሀሳብ ለማቅረብ በማለም ታትሟል።

በመቅደስ እንዳለ
2022-06-06