በአዲስ አበባ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ለሚሰበስቡ 30ሺሕ መምህራንና ተማሪዎች ሽኝት ተደረገ፡፡ የትምህርት ሚንስቴር ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለአንድ ሳምንት እንደሚቋረጥ ተናግሯል፡፡ በዚህ አንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ታዲያ ተማሪዎች እና መምህራን የዘማች ሚሊሻ እና አርሶአደር ሰብል በመሰብሰብ፣ ገንዘብ በማዋጣት፣ ደም በመለገስ እና ስንቅ በማዘጋጀት ለትግሉ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከክልል ትምህርት ቢሮዎች ጋር በመወያየት የወሰነውን ውሳኔ ተከትሎ “ዘመቻ በትምህርት ልማት ግንባር" በሚል መሪ ቃል በዛሬው ዕለት መምህራንና ተማሪዎች የዘማች ቤተሰብ እህል ለመሰብሰብ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እየተሰማሩ ይገኛሉ፡፡ ተማሪዎቹ ተልዕኮአቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ትምህርት ቤቶቻቸው በሚያወጡት የማካካሻ መርሃግብር መሰረት የማካካሻ ትምህርት እንደሚሰጣቸው ጉዳዩን አስመልከቶ ትምህርት ሚንስቴር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡
በሀገሬ ቲቪ
2021-12-06
