የግብርና ሚኒስቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ ካለፈው ዓመት ከ5 ሚሊዮን ኩንታል ያነሰ ሰብል ሰበሰበ። በዘነድሮ መኸር ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ 336 ነጥብ 6 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ተሰብስቧል።ምርቱ አምና በተመሳሳይ ወቅት ከተገኘው 341 ሚሊየን ኩንታል አሽቆልቁሏል።
ይህም የሆነው በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት ምክንያት ማምረት ያልቻሉ ዞኖች እና በትግራይ ክልል ላይ ያለው ሪፖርት ባለመካተቱ እንደሆነ ሪፖርቱ ጠቁሟል። ሚኒስቴሩ ለኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት 374 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ አቅዶ 90 በመቶ ኩንታል ምርት ሰብስቧል።
በመኸር ወቅት 13 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 12 ነጥብ 8 ሚሊየን በዘር መሸፈኑን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-06
