ሀገሬ ቲቪ

በቅርስነት የሚመዘገበው ሆስፒታል

ሀምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል በአዲስ አበባ አስተዳደር በቅርስነት ለመመዝገብ ሂደት ላይ መሆኑ ተሰማ፡፡በዶክትር ካትሪን ሀምሊን እና ባለቤታቸው ዶክተር ሪች ሀምሊን በ1974 የተቋቋመው ሀምሊን ፊስቱላ ሆስፒታል ለበርካታ ልጀገረዶች እና ሴቶች ሕክምና በመስጠት ዘልቋል፡፡

በፊስቱላ የተጎዱ ታካሚዎች አገግመው ሕይወታቸውን ለመምራት እንዲያስችላቸው ከሀያ ዓመት በፊት የገነባው የደስታ መንደር አካባቢውን በአረንጓዴነት በማልማት፣ ስነምህዳሩን በመጠበቅ፣ እና ለህብረተሰቡ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየበትን ዘመን ግምት ውስጥ በማስገባት ለመመዝገብ ሂደት ላይ ነው፡፡

የፊስቱላ ተጠቂዎች በአካላቸውና በስነልቦናቸው ላይ ከሚደርሰው ጉዳት እንዲያገግሙ የተቋሙ አረንጓዴ መሆን እንደሚያግዛቸው ተገልጿል፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-06