ግብጽ ለአፍሪካ ሀገራት 30 ሚሊዮን ዶዝ የኮቪድ-19 ክትባት ልትሰጥ ነው፡፡የግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ከአፍሪካ ሕብረት ጋር በመተባበር ክትባቱን ለመስጠት ቃል ገብተዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት በዋና ከተማዋ ካይሮ እየተካሄደ ባለው የመጀመሪያው የመላው አፍሪካ የጤና ኮንፈረንስ ላይ ነው፡፡በኮንፍረንሱ ላይ ከ100 በላይ ሀገራት የመጡ 400 የሚጠጉ የጤና ባለሙያዎችና ከህክምና ተቋማት የመጡ ተሳታፊዎች ታድመውበታል፡፡
ፕሬዝዳንት ሲሲ ግብፅ እንደሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ውስን ሀብት ቢኖራትም ከሁሉም ጋር ለመተባበር ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-06
