ሀገሬ ቲቪ

እየሰመጡ ያሉ ከተሞች

ከ2015 እስከ 2020 የተነሱ የሳተላይት ምስሎች 99 የባህር ዳርቻ ከተሞች ላይ ትኩረት በማድረግ ምን ያህል ከተሞች እየሰመጡ እንደሆነ አሳይተዋል፡፡በአንዳንድ ከተሞች መሬቱ በዓመት ከ10 ሚሊ ሜትር ወይንም ከ0.4 ኢንች በላይ እየሰመጠ ነው፡፡

የከርሰ ምድር ውኃን ለመጠጥ እና ለሌሎች አገልግሎቶች ማዋል ደግሞ መሬቱ እንዲሰምጥ ምክንያት ሆነዋል ሲል ጥናቱ ይጠቅሳል፡፡በአብዛኛው የእስያ የባህር ዳርቻ ከተሞች እስከ አምስት ሴንቲሜትር ወይም የሦስት ጣት ውፍረት በዓመት እየሰመጡ ነው። በቻይና ውስጥ ቲያንጂን፣ በፓኪስታን ካራቺ እና በፊሊፒንስ ውስጥ ማኒላ ይገኙበታል፤ በ34 ከተሞች ውስጥ ያሉ ቦታዎች በየዓመቱ ከአንድ ሴንቲ ሜትር የሦስት ጣት ውፍረት እጅግ ያነሰ እየሰመጡ እንደሆነ ሳይንስ ኒውስ ዘግቧል፡፡

ከዚህ ቀደም የደቡብ ምስራቅ እስያ ክፍል የሆነችው ጃካርታ በአማካኝ ወደ 30 ሴንቲ ሜትር እየጠለቀች እንደነበር አይዘነጋም ፤ምንም እንኳን መንግሥት በሚወስደው እርምጃ መሻሻል ቢኖርም፡፡

በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-06