የምግብ ዋስትና እጦት በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ላለፉት አስርት ዓመታት የቆዩበት አስከፊ ችግር ነው።
ናይጀሪያን እንኳ ብንመለከት በ1960ዎቹ መጨረሻ በቢያፍራ ጦርነት አንድ ሚሊዮን ሰዎች በረሃብ አለቀዋል።
በጎርጎሮሳውያኑ 1970ዎቹ መጨረሻም በሀገራችን በኢትዮጵያ እንዲሁ በተከሰተው የተፈጥሮ አደጋ የምግብ እጥረት በማጋጠሙ 1 ሚሊዮን ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል።
እነዚህ ክስተቶች በ 80 ዎቹ እና 90 ዎቹ ውስጥም ቀጥለው ቆይተዋል።
ባለፉት አመታት ውስጥ ግን በከፍተኛ የምግብ እጦት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ጋብ ያለ ይመስላል።
በዩክሬን የሚካሄደው ጦርነት በሺሕ በሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮች የራቀ ቢመስልም፤ ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ተፅዕኖው ከፍተኛ እየሆነ መጥቷል። ከዚህ ጋር ተያይዞም በአፍሪካ የምግብ ዋጋ መናር፣ ድህነትን እና ረሃብን እያስከተለ ነው። የእርዳታ ድርጅቶችም ለተረጂዎች የሚያቀርቡትን ምግብ በግማሽ እንዲቀንሱ እያስገደዳቸው ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአውሮፓ ህብረት ባለፈው ዓመት ያሁኑ ቀውስ ከመጀመሩ በፊት የምግብ ዋስትናን የተመለከተ ሪፖርት ይፋ አድርገው ነበር።
እንደ ሪፖርቱ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ የምግብ ዋስትና እጦት አለ ተብሎ ከሚታሰበው 193 ሚሊዮን ህዝብ 2/3ኛ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት ናቸው።
አህጉሪቱ ከምግብ እጦት ባለፈ በዓለም አቀፍ አቅርቦት እጥረት ፣ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ በአየር ንብረት ለውጦችና በውስጣዊ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት እየተናጠች ነው።
የዩኤን የምግብ እና የእርሻ ድርጅት (ኤፍኤኦ) ረዳት ዋና ዳይሬክተር እና የአፍሪካ ተወካይ አቶ አበበ ኃይለ ገብርኤል ለሮይተርስ እንደተናገሩት ጦርነቱ ቀድሞውኑም በአፍሪካ ከፀጥታ ችግርና የምርት እጥረት ጋር በተያያዘ የነበረውን የእህል አቅርቦት ችግር አባብሶታል ብለዋል።
አፍሪካ በተለይ የምግብ አቅርቦቷ በአብዛኛው ከዩክሬን የሚገኝ እንደሆነም አቶ አበበ ተናግረዋል።
እንደ የምግብ እና ግብርና ድርጅት (FAO) መረጃ ቢያንስ 14 የአፍሪካ ሀገራት ግማሹን ስንዴ ከሩሲያ እና ዩክሬን ያስገባሉ።
በመላው አፍሪካ የምግብ ዋጋ መናር ብዙዎች በቀን አንዴ እንኳን ገዝተው እንዳይመገቡ እያደረጋቸው ነው።
ሚሊዮኖችም ለተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተጋልጠዋል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ኤጀንሲ (ኦቻ) ቃል አቀባይ ጄንስ ላርኬ በበኩላቸው በአፍሪካ ሳህል
ቀጠና እስከ 18 ሚሊዮን የሚደርሱ ሰዎች በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ውስጥ ከፍተኛ የምግብ ዋስትና እጦት ይገጥማቸዋል
ብለዋል፡፡ ይህ ቁጥርም ከ2014 ወዲህ ታይቶ አይታወቅም ነው የተባለው።
እንደ ቃል አቀባዩ በሳህል ውስጥ 7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ከ5 አመት በታች ያሉ ህጻናት ለምግብ እጦት ሊዳረጉ ይችላሉበሌላ በኩል የአፍሪካ የግብርና ዘርፍ አወዛጋቢ ነው። በአንድ በኩል አህጉሪቱ ከ 60በመቶ በላይ የዓለም ዓቀፍ የእርሻ መሬቶችን ይዛለች። በአንፃሩ በአግባቡ በመስኖ የሚለማው 6 በመቶው ብቻ ማለትም 13 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ነው።
ግብርና በአፍሪካ ትልቅ አሻራ አለው ። ነገር ግን በሁሉም ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ደረጃዎች ውስጥ ወሳኝ ቢሆንም አብዛኛው ገበሬ በዝናብ ውሃ ላይ የተመሰረተ፣ ትናንሽ ግድቦችን፣ ወንዞችን ጅረቶችን ና የውሃ ጉድጓዶችን በመጠቀም የሚያመርት ነው።
በዚህም አፍሪካ ዝቅተኛ በሆነ ምርታማነቷ ምክንያት ራሷ ማምረት የምትችላቸውን የምግብ ምርቶች ወደ አህጉሪቱ ታስገባለች።
የአፍሪካ የህዝብ ቁጥር እድገት ከዓለም ከፍተኛው ነው። የአህጉሪቱ የህዝብ ቁጥር በ2050 2.3 ቢሊዮን እንደሚደርስ ይገመታል። ይህም ማለት ከሚኖረው አጠቃላይ የዓለም ህዝብ ቁጥር 25 በመቶውን ይሸፍናል ማለት ነው።
ሁኔታው ካልተሻሻለ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ለኑሮ ምቹ ላልሆነ ሁኔታ ተጋላጭ ይሆናሉ።
በፀሃይ ላይ የተመሰረቱ የውሃ ፓምፖች ምርትን እስከ 3 እጥፍ በማሳደግ፣ የመኸር ወቅትን ደግሞ በ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ሄክታር እንደሚያሳድጉ፤ የቤተሰብ ገቢንም እስከ 75 በመቶ እንደሚጨምር ተደርሶበታል።
“ከዚህ ቀደም 200 ኪሎ ግራም እንሸጥ ነበር, እና አሁን 500 ኪ.ግ ሆኗል” ከባለቤቷ እና 4 ልጆቿ ጋር በሩዋንዳ ገጠራማ አካባቢ የምትኖረው የ63 ዓመቷ ሙካምፓራዬ ጄን ተናግራለች።
በመስኖ ላይ የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ለድህነት ቅነሳ አስተዋፅኦ ስለሚያደረጉ እንደሚያደርጉ የዘርፉ ሙራን ይምክራሉ
በዙህም የአፍሪካን የግብርና ዘርፍ ለማዘመን እስከ 65 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ድጋፍ ያስፈልጋል።
በመቅደስ እንዳለ
2022-06-07
