የደንበኞች አገልግሎትን ለማሻሻል ሲባል የክፍያ መንገዶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ማሳወቁን ሰምተናል፡፡የዚህ የቴክኖሎጅ አንድአካል የሆነው
ዘመናዊ ቆጣሪዎችን ወደ ሥራማስገባት መጀመራቸውን የድርጅቱ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ መላኩ ታዬ ነግረውናል፡፡
ከፍተኛበጀትተይዞለትወደ ሥራየገባውና ነባሩንቆጣሪ ወደቀላልና ዘመናዊ የመቀየር ሥራያስፈለገው፣ የኃይልመቆራረጥ ሲኖርለመከታተል እናከዚህ ቀደምከቆጣሪ አንባቢጋር በተያያዘየሚነሳውን የአገልግሎት ተጠቃሚዎች ቅሬታ እንደሚፈታ ታምኖበትነው ተብሏል፡፡
አገልግሎቱን የማዘመን ሥራው ኑርፍሌክስ በተባለ የደቡብኮርያ ኩባንያእየተከናወነ የሚገኝሲሆን በኹለትምዕራፍ ተከፍሎ
ወደ ተግባርየገባው ሲሆን በመጀመርያው ዙር 5 ሺሕየሚሆኑ ቆጣሪዎችን የመግጠም ሥራ እንደሚሰራ እና በኹለተኛው ምዕራፍደግሞ 45 ሺሕየሚሆኑት ነባርቆጣሪዎች በአዲሱ ቴልኖሎጅ የሚተኩ መሆናቸዉን ጨምረው ገልጸዋል፡፡ከዚህበፊት የነበረውቆጣሪ በርካታቅሬታ የሚነሳበት እና ጉድለትያለበት ነው ብለዋል፡፡
ለፕሮጀክቱየገንዘብ ምንጭ የሆነው ከዓለም ባንክበብድር የተገኘሲሆን የገንዘብ መጠኑም 12 ሚሊዮን546 ሺሕ 54 የአሜሪካዶላር ነው፡፡ ቀሪው 9 ሚሊዮን 640 ሺሕ 450 ብር ደግሞበኢትዮጵያ መንግሥትየሚሸፈን እንደሆነ ተገልጿል፡፡
መጋቢት2 ቀን 2014 ዓ.ም ወደ ሥራ የገባውዘመናዊ ቆጣሪዎችን የመቀየር ሥራእስካሁን በአዲስአበባ ብቻ150 የሚሆኑ ቆጣሪዎችመገጠማቸውን ተናግረዋል፡፡ለጊዜዉ ሥራው የተጀመረዉ ከፍተኛ የኃይልተጠቃሚ ለሆኑኢንዱስትሪዎች ብቻ
ነው ብለዋል ዳይሬክተሩ፡፡
በቀጣይበክልሎች በሚገኙኢንዱስትሪዎች ሥራውእንደሚያስፋፋ የተናገሩሲሆን ቴክኖሎጂው በእጅ ስልኮችጭምር መመልከትእና በቀላሉመክፈል እንዲሁም መቆጣጠር የሚቻል በመሆኑየነበሩ ቅሬታዎችን ይቀርፋሉ ተብሎይጠበቃል፡፡
ከዚህ ጋር በተያያዘ ዘመናዊ ቆጣሪየሚጠቀሙ የአፍሪካ ሀገራት ቁጥር ከሁለት የማይበልጡ መሆናቸውን ኃላፊው
ነግረውናል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-07
