በመንግሥት የሥነ ጥበብ ማሠልጠኛ ተቋም የመጀመሪያው የፎቶ ግራፍ ትምህርት ክፍል ተከፈተ፡፡
የአዲስአበባ ባህል ፣ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ፣ ከእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጋር በመተባበር የፎቶ ግራፍ ትምህርት ክፍል እንዲመሠረት ማድረግ መቻሉን ሰምተናል፡፡
የፎቶ ግራፍ የትምህርት ክፍሉ መከፈቱ ለጥበብ ዕድገት የሚኖረው የዕውቀት እና የክህሎት ድርሻ ከፍተኛ ነው ተብሏል፡፡
የቢሮው ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሠርፀ ፍሬስብሐት “ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነ የፎቶ ግራፍ ትምህርት ክፍል፣ በዕይታዊ ጥበብ ሥልጠና ልማዳችን ላይ አንድ እርምጃ ከፍ እንድንል ያደርገናል፤ የፎቶ ግራፍ ጥበብ፣ የፊልም እና የመልቲሚዲያ ጥበባት እናት ጥበብ እንደመሆኑ፣ መሠረቱን በፕሮፌሽናል ሥልጠናዎች ማጽናት ያስፈልጋል።” ብለዋል፡፡
በፍሬህይወት ታደሰ
2022-06-07
